የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዱባይ በተካሄደው የ2026 የአቪዬሽን ስኬት ሽልማት ላይ ሁለት ታላላቅ ሽልማቶችን ተቀዳጀ

© telegram sputnik_ethiopiaየኢትዮጵያ አየር መንገድ በዱባይ በተካሄደው የ2026 የአቪዬሽን ስኬት ሽልማት ላይ ሁለት ታላላቅ ሽልማቶችን ተቀዳጀ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዱባይ በተካሄደው የ2026 የአቪዬሽን ስኬት ሽልማት ላይ ሁለት ታላላቅ ሽልማቶችን ተቀዳጀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 13.06.2026
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዱባይ በተካሄደው የ2026 የአቪዬሽን ስኬት ሽልማት ላይ ሁለት ታላላቅ ሽልማቶችን ተቀዳጀ

አየር መንገዱ ሽልማቶችን የተረከበው በካርጎ እና ሎጅስቲክስ ዘርፍ ባሳየው የላቀ ብቃት ሲሆን በአፍሪካ ደረጃ የዓመቱ ምርጥ የካርጎ አየር መንገድ እና የዓመቱ ምርጥ የኤር ካርጎ ፋርማ አገልግሎት አቅራቢ በመባል ሽልማቶችን ተረክቧል።

የመድኃኒትና ሕክምና ግብዓቶች የጭነት አገልግሎት ሽልማቱ፤ አየር መንገዱ ጥንቃቄና ልዩ ቁጥጥር የሚሹ የሕክምና ምርቶችን በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ጥራት ለማጓጓዝ ያለውን ተዓማኒነትና ብቃት ያረጋገጠበት ነው ተብሏል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ፤ በአህጉሪቱ ያለውን መሪነት ይበልጥ በማጠናከር፣ ወደ ላቀ ከፍታ የመብረርና የመስፋፋት ጉዞውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0