1ኛው የኢትዮጵያ 10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር የፊታችን እሁድ በባህር ዳር ከተማ ሊካሄድ ነው
19:34 12.06.2026 (የተሻሻለ: 19:44 12.06.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
1ኛው የኢትዮጵያ 10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር የፊታችን እሁድ በባህር ዳር ከተማ ሊካሄድ ነው
በውድድሩ ላይ የግል ተወዳዳሪዎችን ጨምሮ ከ6 ክለቦች የተውጣጡ 91 አትሌቶች እሁድ ሰኔ 7 ቀን 2018 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ በሚካሄደው ውድድር እንደሚሳተፉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
የፌዴሬሽኑ ከፍተኛ ቴክኒክ ባለሙያዎች ወደ ስፍራው በማቅናት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እያከናወኑ እንደሚገኙ ተገልጿል።
ውድድሩ ለተተኪ አትሌቶች የውድድር ዕድል ለመፍጠር ያለመ ሲሆን ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ለሚወጡ አትሌቶች የገንዘብ ሽልማት እንደሚበረከት ተመላክቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X