- Sputnik አፍሪካ, 1920
Sovereignty Sources
ዓለም በሉላዊነት ምክንያት ስትተሳሰር ፤ ፕሮግራሙም አፍሪካ ባላት እምቅ የተፈጥሮ ኃብት፣ በማደግ ላይ ባለው የሕዝብ ቁጥሯ ፣ በወጣት ኃይሏ እና በአህጉሪቱ ባሉ አዳዲስ ግኝቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች ያላትን የመወዳደር አቅምና ጥቅም በሰፊው ይዳስሳል፡፡ እንኳን ወደ 'ሶቨርኒቲ ሶርስ' ፕሮግራም በደህና መጡ፣

ዓለም ወደ ባለብዝሃ ወገን የፖለቲካ ስርዓት የምታደርገው ፈጣን ጉዞ

ዓለም ወደ ባለብዝሃ ወገን የፖለቲካ ስርዓት የምታደርገው ፈጣን ጉዞ
ሰብስክራይብ
''ቻይናን፣ ሩሲያና ህንድ የመሳሰሉ ሀገራት የራሳቸውን አሻራ እያስቀመጡ ነው እየመጡ ያሉት፤ ጠንካራ የሚባል ኢኮኖሚ፣ ሰራዊት፣ ዲፕሎማሲ ገንብተዋል። በተለይ ከግሎባል ሳውዝ ሀገራት ጋር ጠንካራ ግንኙነት እየፈጠሩ ነው — የዓለም አቀፍ ፖለቲካዊ ስርዓት ወደ ባለብዙ ወገን ስርዓት እየተለወጠ እንደሆነ ማየት እንችላለን '' ሲሉ በደብረ ማርቆሰ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህር ደረጄ መለስ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው ፕሮግራማችን የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራማችን በክፍል አንድ የዓለም ባለብዙ ዋልታ የዓለም ስርዓትና የወደፊት ዕጣን በተመለከተ በደብረ ማርቆሰ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህር ደረጄ መለስ ጋር እንቃኛለን። በክፍል ሁለት የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት አገራዊ ፖሊሲዎችን ከአህጉሪቱ የጋራ ፍላጎቶች ጋር የማጣጣም አስፈላጊነትን በአርሲ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ አበራ ለሚ ጋር እንዳስሰዋለን።

ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezer Spotify Podcast AddictPocket CastsAfripodsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0