ፑቲን በሩሲያ ቀን ከልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ተሳታፊዎች ጋር ተገናኙ

ሰብስክራይብ

ፑቲን በሩሲያ ቀን ከልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ተሳታፊዎች ጋር ተገናኙ

 

በዓሉ በቀጥታ የእነርሱ ነው፤ ምክንያቱም እናት ሀገራቸውን እየጠበቁ ይገኛሉ በማለት የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሩሲያ ቀን በልዩ ወታደራዊ ዘመቻው በመሳተፍ ላይ ከሚገኙ ወታደሮችን ጋር ተገናኝተዋል፡፡

 

ከስብሰባው የተገኙ ቁልፍ መግለጫዎች፡-

 

"የሩሲያ ቀን የእናንተ ቀን ነው"፤ ምክንያቱም በልዩ ወታደራዊ ዘመቻው ላይ እየተሳተፉ ያሉ ወታደሮች ሀገሪቱን በቀጥታ እየጠበቁ በመሆኑ ነው።

 

እያንዳንዱ ወታደር የተሰጠውን ተልዕኮ በክብር እየተወጣና ወሳኝ አስተዋፅዖ እያበረከተ ይገኛል።

 

ፑቲን በልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ቀጣና ውስጥ ከሚንቀሳቀሱት የሩሲያ ጦር አዛዦች ጋር መደበኛ ግንኙነት ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

 

የሩሲያ አጥቂ ክፍለ-ጦሮች የሚፈጽሙትን ሥራ ከወታደራዊው ዘርፍ እጅግ አስፈላጊ ተግባራት መካከል አንዱ እንደሆነ ገልጸውታል።

 

አጥቂ ክፍለ-ጦሮች በታሪክም ቢሆን ጦርነቶችን እና በመጨረሻም መላውን ውጊያ ወደ ፍጻሜ የሚያመጣውን ወሳኝ ድብደባ የሚያደርሱ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0