የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠናዎች ለኢትዮጵያ የልማት ውጥን መሰረት ናቸው - የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ
16:44 12.06.2026 (የተሻሻለ: 16:54 12.06.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠናዎች ለኢትዮጵያ የልማት ውጥን መሰረት ናቸው - የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ
ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር)፣ የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ተቋማት ብቁ እና ተወዳዳሪ ዜጎችን እንዲያፈሩ ጠንካራ የሪፎርም ሥራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውን በአዲስ አበባ በተከፈተው ዓለም አቀፍ የምርምር ጉባኤ እና የቴክኖሎጂ ውድድር መድረኩ ላይ አንስተዋል።
ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) በጉባኤው የተመረጡ 30 የምርምር ወረቀቶች እና 34 የፈጠራ ሥራዎች ለውድድር ይቀርባሉ ማለታቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል።
ስለሁነቱ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማወቅ ቪዲዮውን ይመልከቱ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X