‘ጉዳዩ ለአፍሪካውያን ለመተው በጣም አደገኛ ነው?’ - ናይጄሪያዊው ምሁር አፍሪካ ከኒውክሌር ውይይቶች መገለሏን አጥብቀው ነቀፉ
10:54 12.06.2026 (የተሻሻለ: 11:04 12.06.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
‘ጉዳዩ ለአፍሪካውያን ለመተው በጣም አደገኛ ነው?’ - ናይጄሪያዊው ምሁር አፍሪካ ከኒውክሌር ውይይቶች መገለሏን አጥብቀው ነቀፉ
ናይጄሪያዊው የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ኤጎሳ ኦሳጋኤ፣ አፍሪካ በዓለም አቀፍ የኒውክሌር ውይይቶች ላይ ግንባር ቀደም ሚና የመጫወት መብት ያላት ሲሆን፣ ደቡብ አፍሪካ የኒውክሌር መርሃ ግብሯን እንድታፈርስ መገደዷ አኅጉሪቱን ሆን ብሎ ለማግለል የተደረገ ማረጋገጫ ነው ማለታቸውን ጠቅሰው የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
የኒውክሌር ታጣቂ አገራት የጦርነት ሰበብ ለማድረግ የኒውክሌር ስርጭትን እንደ ምክንያት መጠቀም የለባቸውም ያሉት ሌላኛው ምሁር ፕሮፌሰር ፌሚ ኦቱባንጆ፤ አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የሚያደርጉት ግፊት ዓላማው ቴህራንን ማዳከም እንጂ የኒውክሌር መሣሪያን ማስቆም እንዳልሆነ አስጠንቅቀዋል።
ከኒውክሌር ጦርነት የሚተርፍ አገር እንደማይኖር ያሳሰቡት ኦቱባንጆ፣ ጨረሩ የፀሐይን ብርሃን እንደሚጋርድ፣ ረሃብን እንደሚያስከትል እና ሰው ሠራሽ የክረምት ቅዝቃዜ እንደሚፈጥር አስገንዝበዋል። በመሆኑም ናይጄሪያ በተባበሩት መንግሥታት በኩል በኒውክሌር ታጣቂ አገራት ላይ ግፊት እንድታደርግ አሳስበዋል።
“አንዴ ጦርነት ከጀመርክ፣ እንዴት እንደሚያልቅ አታውቀውም” ሲሉም ሀሳባቸውን ደምድመዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X