አፍሪካ ፈጣን እና አነስተኛ ቅድመ-ሁኔታ ለታከለበት አጋርነት ፊቷን ወደ ሩሲያ እያዞረች ነው - የምጣኔ ሀብት ባለሙያ

ሰብስክራይብ

አፍሪካ ፈጣን እና አነስተኛ ቅድመ-ሁኔታ ለታከለበት አጋርነት ፊቷን ወደ ሩሲያ እያዞረች ነው - የምጣኔ ሀብት ባለሙያ

ናይጄሪያ በሚገኘው ናምዲ አዚኪዌ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ምሁሩ ዶ/ር ኤድዊን ንዋቹክዉ፣ የአፍሪካ አገራት በለጋሽ እና በተቀባይ መካከል ያለውን የበላይነት እና የበታችነት ተዋረድ ከሚያስቀጥሉት ከተለመዱት የአውሮፓ ኅብረት የትብብር ማዕቀፎች ጋር በተያያዘ ቅሬታ እንዳላቸው ገልፀዋል።

የአውሮፓውያን ጥብቅ ቅድመ-ሁኔታዎች አፍሪካ የፖሊሲ ነፃነት እንደሌላት ተደርጎ የሚወሰደውን አመለካከት የሚያጠናክር ነው ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

ንዋቹክዉ አክለውም “አፍሪካ አውሮፓን እያገለለች ሳይሆን አዳዲስ ውሎችን እየጠየቀች ነው፤ እነሱም፦ ሰፊ የፖሊሲ ነፃነት፣ ፈጣን አፈፃፀም እና ከአፍሪካ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች ጋር የተጣጣሙ አጋርነቶች ናቸው” ብለዋል።

እንደ ኮሜሳ ያሉ የቀጣናው የኢኮኖሚ ማኅበረሰቦች ፊታቸውን ወደ ሩሲያ እያዞሩ ያሉት ሩሲያ በአገር ውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አለመግባት እና ሉዓላዊነትን በማክበር ላይ ትኩረት በማድረግ፣ አነስተኛ የፖለቲካ ቅድመ-ሁኔታዎች ያሉበትን ትብብር ስለምታቀርብ ነው ሲሉ ጠቁመዋል።

የሩሲያ እና አፍሪካ ትስስር ከምዕራባውያን ሥርዓት ውጭ ያሉ ተቋማዊ አማራጮችን በመጨመር የዓለምን ሁለገብ ተለዋዋጭነት ያጠናክራል ሲሉም አክለዋል።

ንዋቹክዉ ሲደመድሙም “ይህ አሠራር ነባሩን ሥርዓት ሙሉ በሙሉ የሚተካ ባይሆንም፣ የእሱን ብቸኛ የበላይነት የሚቀንስ እና በሕጎችና መስፈርቶች ላይ ተጨማሪ ድርድሮች እንዲደረጉ የሚያስገድድ ነው” ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0