ሞስኮ መካከለኛው አፍሪካ እንዲያገግም የእጅ አዙር የቀኝ ግዛት የኢኮኖሚ ሞዴሎች በአስቸኳይ እንዲለወጡ አሳሰበች - በተባበሩት መንግሥታት የሩሲያ ምክትል አምባሳደር

ሰብስክራይብ

ሞስኮ መካከለኛው አፍሪካ እንዲያገግም የእጅ አዙር የቀኝ ግዛት የኢኮኖሚ ሞዴሎች በአስቸኳይ እንዲለወጡ አሳሰበች - በተባበሩት መንግሥታት የሩሲያ ምክትል አምባሳደር

በአፍሪካ የተፈጥሮ ሀብት ላኪ አገራት እና በዓለም አቀፍ ገበያዎች መካከል ያለውን ግንኙነት የሚገዙትና ጊዜ ያለፈባቸው የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት የኢኮኖሚ ሞዴሎች መወገድ አለባቸው ሲሉ አና ኤቭስቲግኔዬቫ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ተናግረዋል።

ከዚህም በተጨማሪ፤ አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የፈጸሟቸው ጠበኛ እርምጃዎች ያስከተሉት መዘዝ በመካከለኛው አፍሪካ አገራት ላይ ተጨማሪ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፈተናዎችን መፍጠሩን፤ በሌላ በኩል ደግሞ የቀጣናው መረጋጋት በቀጠሉት የሽብርተኝነት እንቅስቃሴዎች ምክንያት አሁንም አደጋ ላይ እንደወደቀ ባለሥልጣኗ ጠቁመዋል።

ሩሲያ በመካከለኛው አፍሪካ የሚታዩ አጥፊ አዝማሚያዎችን መመከቷን የምትቀጥል ሲሆን፤ በመላው አህጉሪቱ ደህንነትን ለማጠናከር እንዲረዳም የፀረ-ሽብርተኝነት ልምዷን እንደምታካፍል የሩሲያ ዲፕሎማቷ አፅንዖት ሰጥተው ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0