የሱዳን ተጎጂዎች በአፈና፣ በስቃይ እና በጦርነት ወንጀል ክስ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች በኬንያ ምርመራ እንዲደረግባቸው ጠየቁ

© telegram sputnik_ethiopiaየሱዳን ተጎጂዎች በአፈና፣ በስቃይ እና በጦርነት ወንጀል ክስ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች በኬንያ ምርመራ እንዲደረግባቸው ጠየቁ
የሱዳን ተጎጂዎች በአፈና፣ በስቃይ እና በጦርነት ወንጀል ክስ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች በኬንያ ምርመራ እንዲደረግባቸው ጠየቁ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 10.06.2026
ሰብስክራይብ

የሱዳን ተጎጂዎች በአፈና፣ በስቃይ እና በጦርነት ወንጀል ክስ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች በኬንያ ምርመራ እንዲደረግባቸው ጠየቁ

“ሌጋል አክሽን ወርልድዋይድ” በተባለው ተቋም አማካኝነት የቀረበው ይህ አቤቱታ፣ ከሚያዝያ 2015 እስከ መጋቢት 2017 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ በካርቱም እና በዙሪያዋ የተፈጸሙ የተባሉ ጥሳቶችን ያጠቃልላል።

አሥራ ሁለት ተጎጂዎች በአሁኑ ወቅት በኬንያ ይኖራሉ ተብለው በሚጠረጠሩ 10 የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች አባላት ላይ ክስ እንዲመሠረት ይፈልጋሉ።

የቀረቡት ክሶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

▪ የጅምላ ጭፍጨፋ፣

▪ በማንነት ላይ የተመሠረቱ ወንጀሎች፣

▪ ድብደባ፣

▪ በኤሌክትሪክ ንዝረት ማሰቃየት፣

▪ በቡድን መደፈር፣

▪ አስከሬኖችን በግዳጅ ማጓጓዝ።

እ.ኤ.አ. ከ2023 ጀምሮ ከሱዳን መደበኛ ጦር ጋር ውጊያ ውስጥ የሚገኘው የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ፣ በሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በጦርነት ወንጀል እና በሰብአዊነት ላይ በተፈጸሙ ወንጀሎች መከሰሱ ይታወሳል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0