በኢትዮጵያ የሶላር ፓኔል ማምረቻ ግብዓት ወጪ ንግድ በአንድ ዓመት ውስጥ የ10 እጥፍ ዕድገት አስመዘገበ
በኢትዮጵያ የሶላር ፓኔል ማምረቻ ግብዓት ወጪ ንግድ በአንድ ዓመት ውስጥ የ10 እጥፍ ዕድገት አስመዘገበ
ከፀሐይ ብርሃን የኃይል ማመንጫ ፓኔል ግብዓት ወጪ ንግድ ከዚህ ቀደም ተጨባጭ እንቅስቃሴ ላይ ካልነበረበት ደረጃ በመነሳት እ.ኤ.አ በ2026 የሀገሪቱ አራተኛው ትልቅ የወጪ ንግድ ምርት መሆን መቻሉ ታውቋል።
የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ስታቲስቲክስ መረጃን ዋቢ በማድረግ የወጣው ሪፖርት እንደሚያመላክተው፤ እ.ኤ.አ ከጥር እስከ ግንቦት 2026 ባሉት አምስት ወራት ውስጥ ብቻ ኢትዮጵያ የ99.2 ሚሊዮን ዶላር የሶላር ፓኔል ማምረቻ ግብዓቶችን ወደ ውጭ ልካለች፡፡
ይህም እ.ኤ.አ በ2025 ተመሳሳይ ወቅት ከተመዘገበው የ9.8 ሚሊዮን ዶላር ሽያጭ ጋር ሲነጻጸር የ10 እጥፍ ዕድገት አሳይቷል።
የማምረቻ ግብዓቱ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ገቢ ካስገቡ አስር ቀዳሚ የወጪ ንግድ ምርቶች መካከል ብቸኛው የግብርና ያልሆነ (የኢንዱስትሪ) ምርት በመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ተመዝግቧል፡፡
ይህ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰትና የንግድ ዕድገት የተመዘገበው በውጭ ሀገር ተቋማት በሀገር ውስጥ በሚከናወኑ የማምረቻ ሥራዎች ሲሆን፥ ኢትዮጵያ ለሶላር ኢንዱስትሪው ምቹ የሆነ ታዳሽ ኃይል፣ መሬትና የሰው ኃይል ያላት መሆኑ ለዘርፉ ዕድገት ትልቅ ዕድል መፍጠሩ ተገልጿል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሐዋሳ የመረቁት የቶዮ ሶላር ኢነርጂ ሁለተኛው ምዕራፍ፣ ኦርጅን እና ሉሚንቴክ የሶላር ፋብሪካዎች እንዲሁም የኤች.ዜድ ጋዝ ፋብሪካ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X