የጋራ የደህንነት መፍትሔዎችን ለመቅረጽ ሩሲያ ‘ፍሊት-2026’ ዓለም አቀፍ የባሕር ኃይል ትዕይንት እያስተናገደች ነው - የባሕር ኃይል አዛዥ
17:04 10.06.2026 (የተሻሻለ: 17:14 10.06.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የጋራ የደህንነት መፍትሔዎችን ለመቅረጽ ሩሲያ ‘ፍሊት-2026’ ዓለም አቀፍ የባሕር ኃይል ትዕይንት እያስተናገደች ነው - የባሕር ኃይል አዛዥ
የሩሲያ ባሕር ኃይል ጠቅላይ አዛዥ አድሚራል አሌክሳንደር ሞይሴዬቭ በ“ፍሊት-2026” የባሕር ኃይል ትዕይንት መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ እንደተናገሩት፤ ይህ መድረክ ውይይት ለማድረግ አልያም የሩሲያን ቴክኖሎጂዎች ለማሳየት ብቻ ከመቅረብ ባሻገር፣ አሁን ያሉትን ዓለም አቀፍ የደህንነት ስጋቶች ከውጭ አገር አጋሮች ጋር በጋራ ለመፍታት የሚያስችል መድረክ ነው።
ይህ ዓለም አቀፍ የባሕር ኃይል ትዕይንት ከረቡዕ እስከ እሑድ በሴንት ፒተርስበርግ እየተካሄደ ይገኛል።
በዚህ መድረክ ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ20 በላይ የሚሆኑ የውጭ አገር ልዑካን ቡድኖች እየተሳተፉ መሆናቸውም ታውቋል።
የስፑትኒክ ዘጋቢ ከስፍራው ያጠናቀረው አጭር ተንቀሳቃሽ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X