በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የጠቃሚ ነፍሳት ማራቢያ ማዕከል በይፋ ተመረቀ
15:54 10.06.2026 (የተሻሻለ: 16:04 10.06.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የጠቃሚ ነፍሳት ማራቢያ ማዕከል በይፋ ተመረቀ
ከምስራቅ አፍሪካ ግዙፉ ስለመሆኑ የተነገረለት ይህ ማዕከል ቆቃ በሚገኝ የአበባ ማምረቻ ተቋም ግቢ ውስጥ መገንባቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ (ዶ/ር)፣ ማዕከሉ ቀደም ሲል በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወደ ሀገር ውስጥ ይገቡ የነበሩ ጠቃሚ የነፍሳት ዝርያዎችን በሀገር ውስጥ ለመተካት ያስችላል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ድሪባ ኩማ በበኩላቸው በሰብል ላይ የሚከሰቱ ተባዮችን ለማስወገድ ኬሚካሎችን መጠቀሙ ለሠራተኞች አደገኛ መሆኑን አንስተው፥ ማዕከሉ መቋቋሙ ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ ወሳኝ መሆኑን አስረድተዋል።
ከኬንያ እና ኡጋንዳ በመቀጠል ማምረቻ ማዕከሉን በኢትዮጵያ ያቋቋመው የሬድ ፎክስ ኢትዮጵያ አበባ አምራች ድርጅት፣ ተባይ ተመጋቢ የትል ነፍሳትን እንደሚያመርት መግለፁ ተመላክቷል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X