ምልሰት፦ አፍሪካዊ የእግር ኳስ ኮከብ እግር ኳስን በኮት ዲቯር የጦር መሣሪያዎች ድምፅ ማጥፊያ አድርጎ የተጠቀመበት ታሪክ
15:04 10.06.2026 (የተሻሻለ: 15:14 10.06.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ምልሰት፦ አፍሪካዊ የእግር ኳስ ኮከብ እግር ኳስን በኮት ዲቯር የጦር መሣሪያዎች ድምፅ ማጥፊያ አድርጎ የተጠቀመበት ታሪክ
የ2026ቱን የዓለም ዋንጫ በጉጉት እየተጠባበቅን ባለንበት በዚህ ወቅት፣ ዕውቅናን ለሰላም፣ ስፖርትን ለአንድነት መሣሪያ ያደረገውን አፍሪካዊው የእግር ኳስ ኮከብ ዲዲዬር ድሮግባ ከትዝታ ማሕደር መዝዞ ማውጣት የግድ ይላል።
እ.ኤ.አ. በ2005 ኮት ዲቯር በእርስ በርስ ጦርነት በታመሰችበት በዚያ ወቅት፣ ድሮግባ የአገሩን የመጀመሪያ የዓለም ዋንጫ ተሳትፎ ማረጋገጥ ችሎ ነበር። በወቅቱ በመልበሻ ክፍል ውስጥ ሆኖ በቀጥታ የቴሌቪዥን መስኮት ሥርጭት ላይ ተንበርክኮ ሕዝቡ የጦር መሣሪያውን እንዲያስቀምጥ የተማጽኖ ጥሪ አቀረበ።
የተማፅኖ ውጤቱስ ምን ሆነ?
ጥሪው ተስተጋብቶና ሰሚ አግኝቶ በ2006ቱ የዓለም ዋንጫ ውድድር ወቅት ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ተደረገ። ይህም ስፖርት፣ ለጥቂት ጊዜያት እንኳ ቢሆን፣ የጠመንጃዎችን ድምፅ እንዳይሰማ የማስቻል ታላቅ ኃይል እንዳለው ያስታወሰ የታሪክ አጋጣሚ ነው።
የዓለም ሻምፒዮናዎች ያንን አንድ የሚያደርግ መንፈስ በዚህ ወቅትም በድጋሚ እንዲያንጸባርቁ በእርግጥም መላው ዓለም መሻቱ አያጠያይቅም።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X