"የናሬንድራ ሞዲ አመራር በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን ከድህነት አውጥቷል" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

© telegram sputnik_ethiopia"የናሬንድራ ሞዲ አመራር በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን ከድህነት አውጥቷል" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
የናሬንድራ ሞዲ አመራር በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን ከድህነት አውጥቷል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 10.06.2026
ሰብስክራይብ

"የናሬንድራ ሞዲ አመራር በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን ከድህነት አውጥቷል" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

የኢትዮጵያው መሪ ለሕንዱ አቻቸው በሀገሪቱ ታሪክ ረጅም ዘመን ያገለገሉ ቀዳሚው መሪ መሆን በመቻላቸው የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞዲን “ታላቅ ወንድሜና ውድ ጓደኛዬ” በማለት የገለጿቸው ሲሆን፥ በርዕይና በቁርጠኝነት ዓለም ላይ በሕዝብ ብዛቱ ግዙፍና ንቁ በሆነው የዲሞክራሲ ሥርዓት ውስጥ በተከታታይ ለሦስተኛ ጊዜ ሀገሪቱን በመምራት ታሪካዊ ምዕራፍ በማስመዝገባቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።

"የናሬንድራ ሞዲ አመራር በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን ከድህነት ያወጣ፣ በሕዝብ ደረጃ ዲጂታል ሕዝባዊ መሠረተ ልማትን ያስፋፋና ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ የመሠረተ ልማት ዕድገትን በማስመዝገብ ፈጣን የኢኮኖሚ መሻሻልን ያመጣ" ነው ሲሉ በመጥቀስ አድንቀዋል።

በተጨማሪም ሞዲ ለደቡባዊው ዓለም ድምፅ በመሆን በጽናትና በጥንካሬ እያገለገሉ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስፈሩት የምስጋና መልዕክታቸው ላይ አፅንኦት ሰጥተዋል።

ሞዲ ሕንድን ረዥም ዓመታት የመሩ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን አዲስ ታሪክ አስመዝግበዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ከፍተኛው የኢትዮጵያ የክብር ኒሻን የተበረከተላቸው የመጀመሪያው የሀገር መሪ መሆናቸው ይታወሳል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0