የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ወቅታዊ የደህንነት ሁኔታዎችንና የሳይበር ጥቃት ስጋቶችን ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ የሚያስገድድ አዋጅ ፀደቀ

© telegram sputnik_ethiopiaየኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ወቅታዊ የደህንነት ሁኔታዎችንና የሳይበር ጥቃት ስጋቶችን ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ የሚያስገድድ አዋጅ ፀደቀ
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ወቅታዊ የደህንነት ሁኔታዎችንና የሳይበር ጥቃት ስጋቶችን ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ የሚያስገድድ አዋጅ ፀደቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 10.06.2026
ሰብስክራይብ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር  ወቅታዊ የደህንነት ሁኔታዎችንና የሳይበር ጥቃት ስጋቶችን ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ የሚያስገድድ አዋጅ ፀደቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 24ኛ መደበኛ ስብሰባ፥ ይህን ድንጋጌ ያካተተውንና የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበው ሪፖርትና የውሳኔ ሐሳብ መሠረት የቁልፍ መሠረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት አዋጅን መርምሮ በአዋጅ ቁጥር 1426/2018 በሙሉ ድምፅ አጽድቋል።

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዲማ ነጎዎ (ዶ/ር) ፤ አዋጁ የሳይበር ደህንነት ፕሮግራሞችን ለማስፈጸም፣ ለሥልጠና፣ ለምርምርና ለቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ የሚውል ራሱን የቻለ የቁልፍ መሠረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት ፈንድ በአዲስ ምዕራፍ እንዲደነገግ ማድረጉን ገልፀዋል።

በአዋጁ አፈጻጸምና በቅጣት አወሳሰድ ላይ በመንግሥትና በግል ተቋማት መካከል የነበረው ልዩነት ተሰርዞ ሕጉ በሁለቱም ላይ እኩል ተፈጻሚነት ይኖረዋል፡፡ 

ማንኛውም የመሠረተ ልማት ባለቤት፣ ኃላፊ ወይም ሠራተኛ ሆነ ብሎ ጥፋት ካጠፋ በሕግ እንደሚጠየቅ ተደንግጓል።

ምክር ቤቱ ቁልፍ መሠረተ ልማቶች ለሀገር ሰላምና ሉዓላዊነት ያላቸውን ከፍተኛ ሚና ከግምት ውስጥ በማስገባት ልዩ ጥበቃ እንዲደረግላቸው አዋጁን ማፅደቁ ተገልጿል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0