አርሶ አደሮች ምርታቸውን በዋስትናነት በመጠቀም ከባንኮች መበደር የሚያስችላቸው የዕቃ ማከማቻ ደረሰኝ ሥርዓት ይፋ ሆነ

© telegram sputnik_ethiopiaአርሶ አደሮች ምርታቸውን በዋስትናነት በመጠቀም ከባንኮች መበደር የሚያስችላቸው የዕቃ ማከማቻ ደረሰኝ ሥርዓት ይፋ ሆነ
አርሶ አደሮች ምርታቸውን በዋስትናነት በመጠቀም ከባንኮች መበደር የሚያስችላቸው የዕቃ ማከማቻ ደረሰኝ ሥርዓት ይፋ ሆነ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 10.06.2026
ሰብስክራይብ

አርሶ አደሮች ምርታቸውን በዋስትናነት በመጠቀም ከባንኮች መበደር የሚያስችላቸው የዕቃ ማከማቻ ደረሰኝ ሥርዓት ይፋ ሆነ

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ታዜር ገብረእግዚአብሔር፣ ሥርዓቱ የፋይናንስ ተቋማትን ተሳትፎ የሚያበረታታ መሆኑን፣ ሚኒስቴሩ ከአግራ ጋር በመተባበር በትናንትናው ዕለት ባዘጋጀው የዕቃ ማከማቻ ደረሰኝ ሥርዓት ብሔራዊ መድረክ ላይ ተናግረዋል፡፡

አርሶ አደሩ ምርቱን በፈለገዉ ጊዜና በመረጠዉ ገበያ እንዲያቀርብ የሚያግዝ ሥርዓት መሆኑን ያነሱት ሚኒስትር ዲኤታዉ ይህም የገበያ መረጋጋትን በመፍጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረዉ አስረድተዋል፡፡

"የዕቃ ማከማቻ ደረሰኝ ሥርዓት የሀገሪቱን የግብርና ኢኮኖሚ ለማሸጋገር፣ በገጠር ልማትን ለማጎልበት እና የኅብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትልቅ አቅም ያለው ስትራቴጂካዊ አሠራር ነው።" ብለዋል፡፡

ሥርዓቱን ለመምራት የወጣው ማስፈጸሚያ ደንብና አዲሱ ቦርድ ይፋ የተደረገ ሲሆን፣ ይህም አርሶ አደሩ ገበያ፣ ፋይናንስና ደህንነቱ የተጠበቀ ማከማቻ በአንድ ላይ እንዲያገኝ ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር መገለፁን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia
አርሶ አደሮች ምርታቸውን በዋስትናነት በመጠቀም ከባንኮች መበደር የሚያስችላቸው የዕቃ ማከማቻ ደረሰኝ ሥርዓት ይፋ ሆነ - Sputnik አፍሪካ
1/3
© telegram sputnik_ethiopia
አርሶ አደሮች ምርታቸውን በዋስትናነት በመጠቀም ከባንኮች መበደር የሚያስችላቸው የዕቃ ማከማቻ ደረሰኝ ሥርዓት ይፋ ሆነ - Sputnik አፍሪካ
2/3
© telegram sputnik_ethiopia
አርሶ አደሮች ምርታቸውን በዋስትናነት በመጠቀም ከባንኮች መበደር የሚያስችላቸው የዕቃ ማከማቻ ደረሰኝ ሥርዓት ይፋ ሆነ - Sputnik አፍሪካ
3/3
1/3
2/3
3/3
አዳዲስ ዜናዎች
0