ኢትዮጵያ በኮንትራባንድ ዝውውር ላይ የተሰማሩ ተሽከርካሪዎችን ለመውረስ የሚያስችል የጉምሩክ ማሻሻያ አዋጅ አፀደቀች
20:19 09.06.2026 (የተሻሻለ: 20:24 09.06.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በኮንትራባንድ ዝውውር ላይ የተሰማሩ ተሽከርካሪዎችን ለመውረስ የሚያስችል የጉምሩክ ማሻሻያ አዋጅ አፀደቀች
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ፥ በኮንትራባንድ ዕቃዎች ዝውውር ላይ የተሰማሩ ማናቸውንም ተሽከርካሪዎች ሙሉ በሙሉ ለመውረስ ለሕግ አስከባሪዎችና ለጉምሩክ ባለሥልጣናት ሥልጣን የሚሰጠውን የጉምሩክ አዋጅን እንደገና ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅ አፅድቋል።
የእቅድ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ መነሻ በማድረግ የጸደቀው ይህ ማሻሻያ፤ ቀደም ሲል የነበረው የ100 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ኮንትራባንድን ለመግታት ባለማስቻሉና ሕገ-ወጥ ነጋዴዎች ቅጣቱን እንደ መደበኛ የሥራ ማስኬጃ ወጪ በመቁጠር ድርጊቱን በመቀጠላቸው የተነሳ የተደነገገ ነው ተብሏል።
በተጨማሪም በልዩ ሁኔታ ዕቃ መደበቂያ ተደርገው የተሰሩ፣ የተሻሻሉ፣ ፍጥነት ያላቸው፣ በጫካ ውስጥ የሚጓዙ አልፎ ተርፎም የጥይት መከላከያ የተገጠመላቸው ተሽከርካሪዎች አውቶማቲክ በሆነ መንገድ እንዲወረሱ የተወሰነ ሲሆን፥ ማሻሻያው የሀገርን ገቢ ከመጠበቅ ባሻገር ሕጋዊ የንግድ ሥርዓትንና የጉምሩክ አሰራርን ለማቀላጠፍ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X