የሩሲያው ሮሳቶም የኳንተም ቴክኖሎጂን ለብሪክስ አጋሮቹ ለማካፈል ዝግጁ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገለፁ

ሰብስክራይብ

የሩሲያው ሮሳቶም የኳንተም ቴክኖሎጂን ለብሪክስ አጋሮቹ ለማካፈል ዝግጁ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገለፁ

ሩሲያ ሰባት ቅድሚያ የሚሰጣቸው የኳንተም ኮምፒውተሮች፣ በደርዘን የሚቆጠሩ የኳንተም አልጎሪዝሞች እንዲሁም በኳንተም ኮምፒውቲንግ፣ በሴንሰሮች እና በኮሙዩኒኬሽን ዘርፎች በርካታ ፕሮጀክቶች ያሏት ሲሆን፤ አገሪቱ እነዚህን አቅሞቿ በትብብር አማካኝነት በጥቅም ላይ ለማዋል ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት አሌክሲ ሊካቾቭ በሞስኮ በተካሄደው የመጀመሪያው የብሪክስ ኳንተም ቴክኖሎጂዎች መድረክ ላይ ጠቁመዋል።

ለምን ሮሳቶም ተመረጠ?

ሮሳቶም በኒውክሌር ጣቢያ ፕሮጀክቶች አማካኝነት በውጭ አገራት ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ኢንዱስትሪዎችን በስኬት መገንባቱን ሊካቾቭ ገልጸዋል። ይህ አካሄድ ለኳንተም ጥምረትም ጠቃሚ እንደሚሆን ያምናሉ።

ሊገኝ የሚችለው ዕድል ምንድን ነው?  የብሪክስ የኒውክሌር ኃይል መድረክ ዋና አስተባባሪ ኤልሲ ፑሌ እንዳሉት፦

◾ በሩሲያ የኒውክሌር ኢንዱስትሪ ውስጥ የተጀመረው የመጀመሪያው የኳንተም ኮምፒውቲንግ አተገባበር፤ የኒውክሌር ኃይልን ውጤታማነት እና አስተማማኝነት ማሻሻል እንደሚችል አሳይቷል፤

◾ ሮሳቶም ይህንን የኳንተም ልምድና እውቀት ለዓለም አቀፍ ጥቅም ያካፍላል ተብሎ ይጠበቃል።

በትናንትናው ዕለት (ሰኞ) በሞስኮ የተካሄደው የመጀመሪያው የብሪክስ ኳንተም ቴክኖሎጂዎች መድረክ፣ ተሳታፊዎችን በማገናኘት ስለ ዓለም አቀፉ የኳንተም ውድድር እና ድንበር ተሻጋሪ ትብብሮች ላይ ውይይት እንዲያደርጉ አስችሏል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0