በኡጋንዳ ላይ የተጣለው የኢቦላ የጉዞ ገደብ አላስፈላጊ እና ተገቢ ያልሆነ ነው - የዓለም ጤና ድርጅት

ሰብስክራይብ

በኡጋንዳ ላይ የተጣለው የኢቦላ የጉዞ ገደብ አላስፈላጊ እና ተገቢ ያልሆነ ነው - የዓለም ጤና ድርጅት

በኡጋንዳ የሚገኘውን ዋናውን የኢቦላ የለይቶ ማከሚያ ተቋም የጎበኙት የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ አድኃኖም፣ በኡጋንዳ ላይ የጉዞ ገደብ የጣሉ አገራት ውሳኔያቸውን እንዲያጤኑት አሳስበዋል።

አገሪቱ የተገኙትን ኬዞች (የበሽታውን መኖር) በግልጽ ያሳወቀች እና ተገቢ የሆኑ እርምጃዎችን የወሰደች መሆኑን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ፤ የጉዞ እገዳዎች ግን በሽታውን ለመግታት ውጤታማ ሳይሆኑ በኢኮኖሚ ላይ ጉዳት ያደርሳሉ ብለዋል።

ገደብ የጣሉት የትኞቹ አገራት ናቸው?

ኡጋንዳ በግንቦት ወር የኢቦላ ወረርሽኝ መከሰቱን ካረጋገጠች በኋላ አሜሪካ፣ ካናዳ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና ሌሎችንም ጨምሮ በርካታ አገራት የጉዞ ወይም የዕንቅስቃሴ ገደቦችን ጥለዋል።

የኡጋንዳ ባለሥልጣናት የእነሱን መረጃ ከኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መረጃ ጋር አንድ ላይ ደባልቆ የማቅረቡን አካሄድ የነቀፉ ሲሆን፣ ይህ አሠራር አላስፈላጊ ስጋት መፍጠሩን አንስተዋል። የዓለም ጤና ድርጅትም ከዚያ በኋላ የእያንዳንዱን አገር መረጃ ለይቶ ለማቅረብ የሪፖርት አቀራረቡን አስተካክሏል።

በኡጋንዳ ያለው ተጨባጭ ሁኔታ ምንድን ነው?

ኡጋንዳ በላቦራቶሪ የተረጋገጡ 19 ኬዞችን የመዘገበች ሲሆን፣ አብዛኞቹ ከኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የገቡ ናቸው፤ ከመጀመሪያው የሞት ኬዝ ውጭም በቅርቡ የተመዘገበ ተጨማሪ የሞት አደጋ የለም።

ኡጋንዳ ምን ዓይነት ጥንቃቄዎችን አድርጋለች?

ኡጋንዳ እንደ ተጨማሪ የደህንነት እርምጃ ከኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጋር የሚያገናኙትን የአየር በረራዎች እና የየብስ ድንበር ማቋረጫዎችን አግዳለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0