ናይጄሪያ በሰሜን ምዕራብ የሚገኙ በደርዘን የሚቆጠሩ ነዋሪዎቿ ‘በሰላም ንግግር’ ወጥመድ ከታገቱ በኋላ የማዳን ዘመቻ መጀመሯ ተዘገበ

ሰብስክራይብ

ናይጄሪያ በሰሜን ምዕራብ የሚገኙ በደርዘን የሚቆጠሩ ነዋሪዎቿ ‘በሰላም ንግግር’ ወጥመድ ከታገቱ በኋላ የማዳን ዘመቻ መጀመሯ ተዘገበ

የፖሊስ ኃይሎች በዛምፋራ ግዛት የታገቱትን ነዋሪዎች ያሉበትን ቦታ ለማወቅ እና ለመታደግ የሰው ኃይል እና የስለላ አገልግሎትን በማሰማራት የማዳን ዘመቻ መጀመራቸውን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

በአካባቢው ማኅበረሰቦች ላይ የተጣለውን ገደብ ለማቃለል በማለም፣ ከአሸባሪዎቹ (ሽፍቶቹ) ታዋቂ መሪዎች የአንዱ ዘመዶች ከሆኑ ሰዎች ጋር ለስብሰባ እንዲመጡ ከተጋበዙ በኋላ ቢያንስ 39 ሰዎች መታገታቸውን የዛምፋራ ግዛት ፖሊስ ዕዝ አስታውቋል።

ከተጠለፉት መካከል የተወሰኑት የሽፍቶቹን ጥያቄ ለባለሥልጣናቱ እንዲያደርሱ መለቀቃቸውን መገናኛ ብዙኃን ገልጸዋል።

ቪዲዮው የሚያሳየው 360 ታጋቾችን ነፃ ያወጣውን እና የ‘ሀዲን ካይ’ የፀጥታ ጥረት አካል የሆነውን የቅርብ ጊዜ መጠነ-ሰፊ የማዳን ዘመቻ ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0