ከወራት ወደ ቀናት፦ የቤት ልማትን የሚያፋጥኑ 3 ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች እየተገበሩ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዐቢይ ገለጹ
16:35 09.06.2026 (የተሻሻለ: 16:44 09.06.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ከወራት ወደ ቀናት፦ የቤት ልማትን የሚያፋጥኑ 3 ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች እየተገበሩ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዐቢይ ገለጹ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባን ተከትሎ፣ እጅግ ዘመናዊና ፈጣን የቴክኖሎጂ ግብዓቶችን በመጠቀም የተገነቡ ቤቶች ግንባታ ሳይት ላይ ጉብኝት መደረጉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ፡፡
በግናባታ ቦታው ላይ ሦስት የላቁ የግንባታ ዘዴዎች በጥምረት ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ እነሱም፦
የ3ዲ ህትመት (3D printing)
የቅድመ-ዝግጅት ቀላል የአረብ ብረት ግንባታ እና
የኮንቴይነር መኖሪያ ቤቶች ናቸው።
እንደ ጠቅላይ ሚኒትርሩ ገለጻ፣ ግንባታዎቹ ትክክለኛውን ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ ሲውል ፍጥነት እና ጥራት እርስ በእርስ የማይጋጩ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
“ጥራታቸውን የጠበቁ መኖሪያ ቤቶችን ከወራትና ከዓመታት ይልቅ በጥቂት ቀናት እና ሳምንታት ውስጥ ሰርቶ ማጠናቀቅ እንደሚቻል የታየበት ህያው ምስክር ናቸው።”
ይህ አይነቱ የላቀ ፈጠራ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል በቀላሉ ሊተገበር፣ ሊደገም እና ሊስፋፋ የሚችል በመሆኑ የኢትዮጵያን የቤት ልማት ፕሮግራም አቅጣጫ በከፍተኛ ደረጃ የመቀየር ኃይል አለው ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X