ሩሲያ በ‘ፍሊት-2026’ ዐውደ ርዕይ ላይ ቀጣዩን ትውልድ የባሕር ኃይል ትጥቆቿን ልታሳይ ነው

ሰብስክራይብ

ሩሲያ በ‘ፍሊት-2026’ ዐውደ ርዕይ ላይ ቀጣዩን ትውልድ የባሕር ኃይል ትጥቆቿን ልታሳይ ነው

የሩሲያ መንግሥታዊ የጦር መሣሪያ አምራች ሮሶቦሮንኤክስፖርት በክሮንስታድት፣ ሴንት ፒተርስበርግ ከተማ ሰው አልባ እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት ከሚታዘዙ ጀልባዎች ጀምሮ እስከ ስውር ተዋጊ መርከቦች እና ዘመናዊ አጥቂ ሰርጓጅ መርከቦች ያሉ የተሟሉ አዳዲስ የባሕር ኃይል ፈጠራዎችን ይፋ ያደርጋል።

ሰኔ 3 ቀን ሊጀመር የታቀደው የ‘ፍሊት-2026’ ዓለም አቀፍ አውደ ርዕይ የሚከተሉትን ያካትታል፦

ለመጀመሪያ ጊዜ ለሕዝብ ዕይታ የሚቀርቡ ሰው አልባ ሥርዓቶች ፦ ‘ብሪዝ’ ፣ ‘ቢኢኬ-6’ እና ‘ኦርካን’ የተሰኙ በውኃ ላይ የሚንቀሳቀሱ ሰው አልባ ጀልባዎችን ጨምሮ ‘ኤምኤምቲ-300’ እና ‘ክላቬሲን-1አርኢ’ የተባሉ ራሳቸውን ችለው በውኃ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ለዕይታ ይቀርባሉ። ሁሉም በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዘ ቁጥጥር እና ለድምፅ አልባና ስማርት ክዋኔ የሚረዱ በድብቅ ቴክኖሎጂ የተሠሩ አካላት የተገጠሙላቸው ናቸው።

የባሕር ላይ የጦር መርከቦች – ደምሳሽ እና ስውር ፦ ፕሮጀክት 11356 ኤንጂ ተዋጊ መርከብ (የተቀናጀ የአየር መከላከያ ያለው)፣ የቲግር-ክፍል ኮርቬት (የዛስሎን ራዳር የተገጠመለት)፣ ካራኩርት-ኢ ኮርቬት እና አሌክሳንድራይት-ኢ ፈንጂ አፋሽ መርከብ ይገኙበታል። እያንዳንዳቸው ሰፊ የስውር ቴክኖሎጂ እና ጥልቅ የሮቦቲክስ ውህደት ተደርጎባቸዋል።

የሰርጓጅ መርከብ አቅም – ገዳይ እና ድምፅ አልባ፦ ፕሮጀክት 636 እና 677ኢ አሙር-1650 ዲዚል-ኤሌክትሪክ ሰርጓጅ መርከቦች ናቸው። እነዚህ መርከቦች የቶርፒዶ እና የሚሳይል የማጥቃት አቅምን እጅግ ከተቀነሰ የድምፅና ራዳር አሻራ፣ እንዲሁም ረጅም ሰዓት በውኃ ውስጥ የመቆየት ብቃት ጋር ያቀናጁ ናቸው።

የባሕር ጠረፍ መሣሪያዎች – ለጦርነት ዝግጁ እና የተፈተኑ፦ ሩቤዥ-ኤምኢ የሚሳይል ሥርዓት እና በሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር፣ በደህንነተ አገልግሎት እና በአደጋ ጊዜ ሚኒስቴር ውስጥ በአሁኑ ወቅት በንቁ አገልግሎት ላይ የሚገኙ ሙሉ የትጥቅ ዓይነቶች ይቀርባሉ።

ከአጋር አገራት የባሕር ኃይሎች ጋር 75 ገለጻዎች እና ውይይቶች የተያዙለት በመሆኑ፣ ሮሶቦሮንኤክስፖርት የሩሲያን የባሕር ላይ ወታደራዊ የወጪ ንግድ እና የቴክኖሎጂ ነፃነትን በግልጽ እያጠናከረ መሆኑን ያሳያል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0