ሰርግ እና ምረቃት ሲገጥም - በአንድ ጀንበር ድርብ ተልዕኮ የተቀበለው ጀማሪ መኮንን
14:44 09.06.2026 (የተሻሻለ: 15:04 09.06.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሰርግ እና ምረቃት ሲገጥም - በአንድ ጀንበር ድርብ ተልዕኮ የተቀበለው ጀማሪ መኮንን
በሁርሶ ዕጩ መኮንን ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የ27ኛ ዙር ፅናት ኮርስ ተመራቂው ምክትል መቶ አለቃ አዲስ ብርሃኑ ከፍቅር አጋሩ ከወይዘሮ ሰላም ታረቀኝ ጋር በዕጩ መኮንኖች የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ዕለት የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ጋብቻቸውን ፈጽመዋል።
የማሠልጠኛ ትምህርት ቤቱ አዛዥ ኮሎኔል ከድር ጫጮ፣ ሙሽራው የጀማሪ መኮንንነት ሥልጠናውን አጠናቆ ለምረቃ በበቃበት ወቅት ጋብቻ መፈጸሙ የሃገርም የቤተሰብም ድርብ ኃላፊነት መቀበሉን እንደሚያሳይ ጠቅሰው መልካም ጋብቻ እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል።
ሙሽሮቹ ማሰልጠኛ ተቋሙ ባደረገላቸው የሰርግ ፕሮግራም መደሰታቸውን መግለጻቸውን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ አጋርቷል፡፡
የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ማሰልጠኛ እና የሁርሶ ዕጩ መኮንን ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቶችም ለጥንዶቹ የጋራ ስጦታ አበርክተውላቸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

1/2
© telegram sputnik_ethiopia

2/2
© telegram sputnik_ethiopia
1/2
© telegram sputnik_ethiopia
2/2
© telegram sputnik_ethiopia