የሱዳን ግጭት በሠራዊቱ የበላይነት መያዝ ምክንያት መልክ እየቀየረ ነው፤ የፈጥኖ ደራሽ ኃይል አማፂያን ደግሞ አውዳሚ ድሮን ስልቶችን እየተጠቀሙ ነው - ባለሙያ

ሰብስክራይብ

የሱዳን ግጭት በሠራዊቱ የበላይነት መያዝ ምክንያት መልክ እየቀየረ ነው፤ የፈጥኖ ደራሽ ኃይል አማፂያን ደግሞ አውዳሚ ድሮን ስልቶችን እየተጠቀሙ ነው - ባለሙያ

በኮርዶፋን፣ በዳርፉር እና በብሉ ናይል ቀጣናዎች በቅርቡ የተባባሰው ጦርነት ስለ ግጭት አፈታት የሚነሱ ውይይቶችን ዳግም እንዲያንሰራሩ ቢያደርግም፤ ሁለቱም ወገኖች ወደ ድርድር ከመምጣት ይልቅ ይበልጥ አቋማቸውን በማጠናከር ላይ እንዳተኮሩ የሱዳን ቀውስ ባለሙያ አሚን ኢስማኢል ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

የግዛቶች ቁጥጥር አሁንም የተረጋጋ ባይሆንም፣ የአማፂው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል የሀብት አቅርቦት እየመነመነ መምጣቱን ተከትሎ የአገሪቱ ብሔራዊ ሠራዊት ቡድኑ ለወራት ተቆጣጥሯቸው በነበሩ አካባቢዎች ላይ የበላይነቱን ለመያዝ አስችሎታል ሲሉ አብራርተዋል።

በተጨማሪም ኢስማኢል የድሮን ውጊያ ግጭቱን መልክ እንዳስቀየረው አስጠንቅቀዋል።

አማፂ ቡድኑ በኋይት ናይል እና በደቡብ ኦምዱርማን በሚገኙ የመኖሪያ አካባቢዎች እና መሠረተ ልማቶች ላይ የሚያካሂደው የድሮን ጥቃት፤ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዳይመለሱ ለማደናቀፍ እና ኢኮኖሚውን ሽባ ለማድረግ ሆን ተብሎ ሲቪሎችን ለማሸበር የሚደረግ ነው ብለዋል።

ቪዲዮው የሚያሳየው በሰሜን ኮርዶፋን ኤል ኦቤይድ በሚገኝ የነዳጅ ማደያ ላይ በቅርቡ በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ድሮን የተሰነዘረውን ጥቃት ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0