የሩሲያ ኩባንያዎች ታንዛኒያ ውስጥ ክትባቶችን ለማምረት ዝግጁ ናቸው - ዶዶማ

ሰብስክራይብ

የሩሲያ ኩባንያዎች ታንዛኒያ ውስጥ ክትባቶችን ለማምረት ዝግጁ ናቸው - ዶዶማ

 

ዋና ዋና የሩሲያ የፋርማሲዩቲካል ተቋማት ከታንዛኒያ ጋር በመተባበር በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት 20 ሚሊዮን የሚደርሱ የክትባት መጠኖችን (ዶዞችን) ማምረት እንደሚችሉ የታንዛኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዓለም አቀፍ ንግድ እና ኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ዳይሬክተር ጆን ኡላንጋ ለመገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።

ከሩሲያ ጋር በመተባበር የሚበለጽጉት ክትባቶች ለሀገር ውስጥ ጥቅም እና ለሌሎች ቀጣናዊ ገበያዎች እንደሚሰራጩ የገለጹ ሲሆን ለየትኞቹ ልዩ በሽታዎች የታሰቡ እንደሆኑ ግን አልጠቀሱም።

የሩሲያ-ታንዛኒያ የትብብር ዘርፎች ከጤና ጥበቃ በተጨማሪ እንደ ዩራኒየም እና ኒኬል ያሉ ወሳኝ ማዕድናትን ማውጣት እና የኢነርጂ ዘርፎችን እንደሚያካትቱ ዲፕሎማቱ ጠቁመዋል።

በተጨማሪም የሩሲያ ኩባንያዎች በታንዛኒያ የነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ ክምችቶችን የመፈለግ እና የማልማት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0