ዘለንስኪ ለዓለም ያሠራጨው ጽሁፍ ተገቢ አልነበረም - ላቭሮቭ
ለቭላድሚር ፑቲን የተጻፈው ነገር ግን ለመላው ዓለም የተበተነው ረጅም "ጽሁፍ" አካሄዱ ተገቢ ያልነበረና ዘለንስኪ ድርድር እንደማይፈልግ ያሳየበት ነው ሲሉ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በሞስኮ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል።
ከዩክሬን ጋር ውይይቶችን እንደገና መጀመርን በተመለከተ ፑቲን በሴንት ፒተርስበርግ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ፎረም በቂ ምላሽ እንደሰጡበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።
ዘለንስኪ በቅርቡ ለሩሲያ ፕሬዚዳንት በላከው ደብዳቤ፤ ቀጥተኛ ንግግሮች እንዲቀጥሉ፣ "ግጭቱ" እንዲቆም እና የጦር እስረኞች ልውውጥ እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል። ፑቲን በ #SPIEF ጠቅላላ ጉባኤ በሰጡት ምላሽ ደብዳቤው ትዕቢት የታከለበት እንደነበር አጽንኦት ሰጥተዋል።
ክሬምሊን በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ፤ ኪየቭ ሕፃናት ላይ የሽብር ጥቃት እየፈጸመች ስለ ዩክሬን የሰላም ድርድር ማውራት አዳጋች እንደሆነ አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X