ቤላሩስ በጋና በኩል በምዕራብ አፍሪካ ጠንካራ መሠረት እንዲኖራት ትፈልጋለች - የቤላሩስ ፕሬዚዳንት

ሰብስክራይብ

ቤላሩስ በጋና በኩል በምዕራብ አፍሪካ ጠንካራ መሠረት እንዲኖራት ትፈልጋለች - የቤላሩስ ፕሬዚዳንት

አሌክሳንደር ሉካሼንኮ፤ የቤላሩስን የግብርና ልምድ እና ቴክኖሎጂ በማጋራት ጋና የምግብ ዋስትናዋን እንድታረጋግጥ ለመርዳት እንዲሁም ወታደራዊ-ቴክኒካዊ ትብብር እና የባለሙያዎች ሥልጠና ለማስፋፋት ቃል ገብተዋል። በምላሹም ቤላሩስ የተረጋጋ የኮኮዋ ምርት ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት እና ጋና ውስጥ ለሸቀጦቿ የሎጂስቲክ ማዕከል ለማግኘት እንደምትፈልግ ከጋና አቻቸው ጆን ድራማኒ ማሃማ ጋር ባደረጉት ውይይት ገልጸዋል።

ሁለቱ ሀገራት ውይይቱን ተከትሎ የተለያዩ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል፦

▪ የንግድ እና የኢኮኖሚ ትብብር የጋራ ኮሚቴ ለማቋቋም፣

▪ የዲፕሎማሲ እና የአገልግሎት ፓስፖርት ላላቸው ዜጎች የነጻ ቪዛ እንቅስቃሴ መብት፣

▪ በግብርና ትብብር ዙሪያ የጋራ መግባቢያ ሰነድ።

"በአፍሪካ ያለን እንቅስቃሴ እና የሥራችን ዋና ፍልስፍና እኛ አዲስ ቀኝ ገዢዎች አይደለንም — ወደ እናንተ የመጣነው እንደ ወዳጅ ነው የሚል ነው" ሲሉ ሉካሼንኮ አጽንኦት ሰጥተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0