የኮንጎ ባለሥልጣናት የኢቦላ ስርጭት ሊባባስ እንደሚችል አስጠነቀቁ

© telegram sputnik_ethiopiaየኮንጎ ባለሥልጣናት የኢቦላ ስርጭት ሊባባስ እንደሚችል አስጠነቀቁ
የኮንጎ ባለሥልጣናት የኢቦላ ስርጭት ሊባባስ እንደሚችል አስጠነቀቁ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 08.06.2026
ሰብስክራይብ

የኮንጎ ባለሥልጣናት የኢቦላ ስርጭት ሊባባስ እንደሚችል አስጠነቀቁ

በቡንዲቡግዮ የኢቦላ ወረርሽኝ ዝርያ ዙሪያ የተሰሙ የቅርብ ጊዜ መረጃዎች፦

ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ

▪ የኮንጎ ጤና ሚኒስቴር ግንቦት 29 ቀን ባወጣው ሪፖርት፤ “ተገቢ የሆኑ እርምጃዎች በአስቸኳይ ካልተወሰዱ የሕመምተኞች ቁጥር ሊጨምር ይችላል” ሲል አስጠንቅቋል።

▪ የሀገሪቱ የጤና ባለሥልጣናት ከግንቦት 6 እስከ 15 ባለው ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በበሽታው መያዛቸው መረጋገጡ፤ “ከአንድ የጋራ ምንጭ ከፍተኛ የመጋለጥ እና የሥርጭት ሁኔታ መኖሩን” ይጠቁማል ብለዋል።

▪ በወረርሽኙ እንደተያዙ የተረጋገጡ ሰዎች ቁጥር 515 የደረሰ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 91 የሚሆኑት ሕይወታቸው ማለፉን ባለሥልጣናቱ ጨምረው ገልጸዋል።

▪ ሦስት ተጨማሪ ታካሚዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው የዳኑ ሰዎች ቁጥር 12 ደርሷል።

ኡጋንዳ

▪ በሳምንቱ መጨረሻ ሦስት አዳዲስ የኢቦላ ጉዳዮች መመዝገባቸውን ተከትሎ አጠቃላይ በቫይረሱ እንደተያዙ የተረጋገጡ ሰዎች ቁጥር 19 መድረሱን የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ቅዳሜ አስታውቋል።

▪ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ አድኃኖም የኡጋንዳን ጠንካራ አመራር እና የድንበር ተሻጋሪ ትብብር አወድሰዋል።

የበሽታ መከላከል ምላሽ

▪ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ በሀገሪቱ የመከላከያ እርምጃዎችን ለማጠናከር 19.5 ሚሊዮን ዶላር እንደምታንቀሳቅስ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

▪ ዚምቧቤ ለአፍሪካ ኅብረት የጤና ኤጀንሲ አፍሪካ ሲዲሲ 1 ሚሊዮን ዶላር እንደምትለግስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሞን ሙርዊራ ይፋ አድርገዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0