የፓስፖርት አገልግሎትን ከፋይዳ ጋር እያቀናጀ እንደሚገኝ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አስታወቀ

ሰብስክራይብ

የፓስፖርት አገልግሎትን ከፋይዳ ጋር እያቀናጀ እንደሚገኝ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አስታወቀ

ውህደቱ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን መሠረት ያደረገ እንደሆነ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ገልጸዋል።

ይህም ፓስፖርት ማውጣትን ቀላል በማድረግ፤ ዜጎች ባሉበት ቦታ ሆነው በዲጂታል ቴክኖሎጂ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል እንደሆነ ተነግሯል።

አሠራሩ፤ “ተገልጋዮች ዐሻራ ለመስጠት በአካል መገኘት ሳያስፈልጋቸው፤ በፋይዳ ሲስተም ላይ ያለውን መረጃ በቀጥታ በመጠቀም አገልግሎቱን በኦንላይን ብቻ እንዲያጠናቅቁ ያስችላቸዋል” ብለዋል።

ተቋሙ እያካሄደ ያለውን ለውጥ በማስቀጠል፤ የተገልጋዮችን እንግልት ለማስቀረት የሚያደርገውን ጥረት እንደሚያጠናክር ኃላፊዋ ጨምረው ገልጸዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0