አልጄሪያ ለመጀመሪያው የድሮን አብራሪዎች ማሠልጠኛ ማዕከል ሕጋዊ ፈቃድ ሰጠች

ሰብስክራይብ

አልጄሪያ ለመጀመሪያው የድሮን አብራሪዎች ማሠልጠኛ ማዕከል ሕጋዊ ፈቃድ ሰጠች

በመንግሥት የሚተዳደረው የኢንዱስትሪ ቴክኖሎጂዎች ምርምር ማዕከል፤ ስካይ-ቴክ ኢንጂነሪንግ በተሰኘው ተቀጥላ ኩባንያው አማካኝነት በምድብ 1 እና 2 ስር የድሮን አብራሪዎችን ለማሠልጠን የመጀመሪያውን የአልጄሪያ የዕውቅና ማረጋገጫ ፈቃድ አግኝቷል።

የማዕከሉ ዳይሬክተር ዶክተር ሪያድ ባጂ፤ የዕውቅና ማረጋገጫው የተገኘው ከዓመታት የቴክኒክ እና የሕግ ማሟያ ሥራዎች በኋላ መሆኑን ገልጸው፤ "ድሮን ማብረር የሚፈልግ ማንኛውም ሰው መሠልጠን፣ መገምገም እና የብቃት ማረጋገጫ ማግኘት አለበት" ብለዋል።

ሥልጠናው ለትርፍ ጊዜ አብራሪዎች ከ8 እስከ 10 ቀናት የሚወስድ ሲሆን ለባለሙያዎች ደግሞ እስከ ሁለት ወር ይደርሳል።

ማዕከሉ፤ ሥልጠናው በመሬት ካርታ ዝግጅት፣ በሰብል ክትትል እና በትክክለኛ የዕፅዋት እንክብካቤ ለግብርናው ዘርፍ ከፍተኛ የምጣኔ ሀብት ተፅዕኖ ይኖረዋል ብሎ እንደሚጠብቅ ገልጿል።

የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ባልደረባ የሆኑት ፕሮፌሰር መሐመድ ቡሂቻ፤ ሌሎች ተቋማትም ዕውቅና ለማግኘት በማመልከት ላይ መሆናቸውን ጠቁመው፤ "ዕውቅና ከተሰጣቸው ማዕከላት የምስክር ወረቀት ያላገኘ ማንኛውም አብራሪ ድሮን እንዲያበር አይፈቀድለትም" ሲሉ አክለዋል።

ተንቀሳቃሽ ምሥሉ ድሮኖች ቻይና ውስጥ ዘር ሲዘሩ እና በሰብሎች ላይ ኬሚካል ሲረጩ ያሳያል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0