የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ለመጀመሪያው የውጭ ኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ ሰጠ

© telegram sputnik_ethiopiaየኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ለመጀመሪያው የውጭ ኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ ሰጠ
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ለመጀመሪያው የውጭ ኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ ሰጠ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 08.06.2026
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ለመጀመሪያው የውጭ ኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ ሰጠ

የኢንቨስትመንት ፈቃዱን ያገኘው የናይጄሪያው ዩናይትድ ካፒታል ግሩፕ ተቀጥላ ኩባንያ የሆነው ዩናይትድ ካፒታል ፋይናንሻል ሰርቪስ ነው።

ተቋሙ በሕግ ከተቀመጠው የ25 ሚሊዮን ብር አነስተኛ ካፒታል በላይ ከ1.5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ አስገብቶ ነው የሀገሪቱን የካፒታል ገበያ የተቀላቀለው።

ፈቃዱ የሀገሪቱን የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ጠቅላላ ቁጥር ወደ አስራ ስምንት እንዲሁም የኢንቨስትመንት ባንኮችን ቁጥር ወደ ሰባት ከፍ እንዳደረገው የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን በማኅበራዊ ገጹ አስታውቋል።

"እንደ ዩናይትድ ካፒታል ያለ የፓን-አፍሪካዊ ተቋም ወደ ገበያው መግባቱ በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ዕድገት ላይ ታሪካዊ ምዕራፍ ነው" ሲሉ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሃና ተኸልቁ በይፋዊ የፈቃድ አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተናግረዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0