የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት "ኢቲቱ" የተሰኘ ወተት የሚያረጋ ፕሮ ባዮቲክ እርሾ ይፋ አደረገ
12:21 08.06.2026 (የተሻሻለ: 12:24 08.06.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት "ኢቲቱ" የተሰኘ ወተት የሚያረጋ ፕሮ ባዮቲክ እርሾ ይፋ አደረገ
ተቋሙ የባዮ ቴክኖሎጂ ምርምር ውጤቱን የዓለም የወተት ቀንን አስመልክቶ በተዘጋጀ መድረክ ላይ አስተዋውቋል።
"ኢቲቱ" እርሾ ፓስቸራይዝድ የተደረገ ወተትን በአራት ሰዓታት ውስጥ እንደሚያረጋ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ንጉሴ ደቻሳ፤ “እርሾው በሀገሪቱ ያሉ የወተት ማቀነባበሪያ ድርጅቶች በውጭ ምንዛሪ ከውጭ አስገብተው የሚጠቀሙበትን እርሾ የሚተካ ነው” ማለታቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች ዘግበዋል።
ምርቱ ለምግብ ዋስትና እና ለጤንነት ወሳኝ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን የያዘ ነውም ተብሏል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለጸገ መሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X