የአፍሪካ ፍርድ ቤት ታንዛኒያ ለግድያ ወንጀል የምትጥለውን አስገዳጅ የሞት ቅጣት እና ስቅላት እንድትሽር አዘዘ
11:41 08.06.2026 (የተሻሻለ: 11:44 08.06.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ፍርድ ቤት ታንዛኒያ ለግድያ ወንጀል የምትጥለውን አስገዳጅ የሞት ቅጣት እና ስቅላት እንድትሽር አዘዘ
ፍርድ ቤቱ በሰጠው ውሳኔ፤ አስገዳጅ የሞት ቅጣት ታንዛኒያ ካጸደቀችው የአፍሪካ የሰብዓዊና የሕዝቦች መብቶች ቻርተር ጋር የሚጋጭ እና በቻርተሩ የተረጋገጠውን በሕይወት የመኖር መብት ጨምሮ መሠረታዊ የሰብዓዊ መብቶችን የሚጥስ ነው ብሏል።
በታንዛኒያ ማረሚያ ቤቶች ውስጥ ቅጣታቸውን የሚጠባበቁ ሰባት የሞት ፍርደኞች፤ በሕይወት የመኖር፣ የሰብዓዊ ክብር፣ ፍትሐዊ ዳኝነት የማግኘት፣ የሕግ ውክልና የማግኘት እና ጉዳያቸው በአስቸኳይ የመታየት መብቶቻቸው ተጥሷል በማለት፤ ሦስት የተለያዩ አቤቱታዎችን አቅርበዋል።
ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ ያቀረቡትን የካሳ እና ከእስር የመፈታት ጥያቄ ውድቅ ቢያደርግም፤ አስገዳጅ የሞት ቅጣት እና በስቅላት መገደል እንዲሻር ያቀረቡትን ቀዳሚ አቤቱታ እንደተቀበለ የአመልካቾቹ ጠበቃ አማኑኤል ሱድ ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X