ፖርት ሱዳን ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ ወዲህ የመጀመሪያውን ትልቅ ባሕላዊ ዝግጅት ማስተናገዷን የሩሲያ ኤምባሲ አስታወቀ
18:59 07.06.2026 (የተሻሻለ: 19:04 07.06.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ፖርት ሱዳን ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ ወዲህ የመጀመሪያውን ትልቅ ባሕላዊ ዝግጅት ማስተናገዷን የሩሲያ ኤምባሲ አስታወቀ
ከግንቦት 27 እስከ 30 በፖርት ሱዳን በሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ የተዘጋጀ የሥነ-ጥበብ አውደ-ርዕይ፤ የስላቪክ ሥነ-ጽሁፍ እና ባሕል ቀን እንዲሁም የሩሲያ ቋንቋ ቀንን አስቦ ውሏል። ይህም በሚያዝያ ወር 2015 ዓ.ም ግጭቱ ከተቀሰቀሰ ወዲህ በጊዜያዊቷ ዋና ከተማ የተካሄደ የመጀመሪያው ባሕላዊ ዝግጅት ነው።
በአውደ-ርዕዩ ላይ ስዕሎች፣ የሩሲያ ክላሲካል ሙዚቃ ትርዒቶች እና ዘጋቢ ፊልም ቀርቧል።
ዲፕሎማቶች፣ ወታደራዊ አታሼዎች፣ የሱዳን ባለሥልጣናት እና የአካባቢው ዜጎች በተገኙበት በዚህ ሁነት፤ ከፍተኛ የሕዝብ ፍላጎት እንደነበርና ለሩሲያ ቋንቋ እና ባሕል ያለውን አድናቆት ይበልጥ ማሳደጉን ኤምባሲው አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X