ከቪዛ ነፃ እንቅስቃሴ ‘ለአፍሪካ እውነተኛ ውህደት’ መንገድ እንደሚጠርግ ካሜሩናዊው ባለሙያ ገለጹ
16:40 07.06.2026 (የተሻሻለ: 16:44 07.06.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ከቪዛ ነፃ እንቅስቃሴ ‘ለአፍሪካ እውነተኛ ውህደት’ መንገድ እንደሚጠርግ ካሜሩናዊው ባለሙያ ገለጹ
የአፍሪካ መሪዎች ውህደቱን ለማፋጠን እርምጃዎችን ሲወስዱ "ሊበረታቱና ሊደገፉ ይገባል" ሲሉ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ተመራማሪው ዴቪድ ሜልቪን ኤቡቱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
አሁን እንደ ቶጎ እና ኮንጎ ሪፐብሊክ ያሉ ሀገራት ለሁሉም የአፍሪካ ዜጎች ከቪዛ ነፃ መብት አውጀዋል፤ ካሜሩንም ከኮትዲቯር ጋር የነፃ እንቅስቃሴ ስምምነት ለመፈረም ተዘጋጅታለች፡፡ ይህ እንደ ባለሙያው አስተያየት "የሚደነቅ ተነሳሽነት" ነው።
ኤቡቱ፤ የአፍሪካ መሪዎች ይህ ውጥን "እውን እና ውጤታማ እንዲሆን ከማንኛውም ዓይነት ውጫዊም ሆነ ውስጣዊ ጫና ራሳቸውን ነፃ እንዲያወጡ" ጥሪ አቅርበዋል።
በተጨማሪም ፓን-አፍሪካኒዝም በንግግር ብቻ የተገደበ መሆን እንደሌለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።
"ለረጅም ጊዜ የአፍሪካ ውህደት ጉዳይ ከቃላት ያላለፈ የንግግር ማድመቂያና ባዶ መፈክር ሆኖ ቆይቷል" ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X