ኢትዮጵያ የኢቦላ ወረርሸኝ መከላከል ዝግጁነቷን በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ የባለሙያዎች የተግባር ልምምድ አጠናከረች

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የኢቦላ ወረርሸኝ መከላከል ዝግጁነቷን በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ የባለሙያዎች የተግባር ልምምድ አጠናከረች

አዲሱ የኢቦላ ቫይረስ ወረርሽኝ በኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና ኡጋንዳ መከሰቱን ተከትሎ፤ ጥብቅ የቅኝትና የልየታ ሥራ እየሠራ እንደሆነ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፤ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ የጤና ልየታ፣ የቁጥጥር፣ የቅኝት ሥራዎች ላይ ትኩረት ያደረገ የባለሙያዎች ተግባራዊ ልምምድን ቃኝተዋል።

በዚህ ወቅት ባደርጉት ንግግር በእየርከኑ የሚገኙ የጤና ተቋማት እና የጤና ባለሙያዎች ወረርሽኙን ለመከላከል ዝግጁ እንዲሆኑ አሳስበዋል።

ኢትዮጵያ በአየርም ሆነ በየብስ በሚገኙ የመግቢያና መውጫ በሮች በኩል በሽታው ከተከሰተባቸው ሀገራት በሚመጡ ተጓዦች ላይ የተላላፊ በሽታዎች ቁጥጥርና ቅኝት ሥራዎችን አጠናክራ እንደቀጠለች ተገልጿል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0