አዲስ አበባ 19ኛውን የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን አስተናገደች
11:31 07.06.2026 (የተሻሻለ: 11:34 07.06.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
አዲስ አበባ 19ኛውን የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን አስተናገደች
መነሻ እና መድረሻውን መስቀል አደባባይ በማድረግ በተካሄደው ውድድር፤ በወንዶች የሸገር ሲቲው አትሌት ጌታቸው ማስረሻ፤ በሴቶች ደግሞ የአዲስ አበባ ፖሊሷ መሰለች አለማየሁ አሸናፊ ሆነዋል።
በ19ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን በወንዶች 455 እና በሴቶች 183፤ በድምሩ 638 አትሌቶች ተሳትፈዋል።
የውድድሩ ዋና አላማ በዴንማርክ ኮፐንሃገን በመስከረም ወር 2019 ዓ.ም ለሚካሄደው 26ኛው የዓለም አትሌቲክስ የግማሽ ማራቶን ሻምፒዮና ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች መምረጥ እና ተተኪዎችን ማፍራት እነደሆነ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X