SPIEF አፍሪካ የምዕራባውያንን ሥርዓቶች ችላ በማለት የፋይናንስ ሉዓላዊነት የምትጎናጸፍበትን መንገድ ይጠቁማል - ኢትዮጵያዊ ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopiaSPIEF አፍሪካ የምዕራባውያንን ሥርዓቶች ችላ በማለት የፋይናንስ ሉዓላዊነት የምትጎናጸፍበትን መንገድ ይጠቁማል - ኢትዮጵያዊ ባለሙያ
SPIEF አፍሪካ የምዕራባውያንን ሥርዓቶች ችላ በማለት የፋይናንስ ሉዓላዊነት የምትጎናጸፍበትን መንገድ ይጠቁማል - ኢትዮጵያዊ ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 07.06.2026
ሰብስክራይብ

SPIEF አፍሪካ የምዕራባውያንን ሥርዓቶች ችላ በማለት የፋይናንስ ሉዓላዊነት የምትጎናጸፍበትን መንገድ ይጠቁማል - ኢትዮጵያዊ ባለሙያ

በሩሲያ በተካሄደው #SPIEF2026 ላይ የነበረው የአፍሪካ ሀገራት ተሳትፎ፤ አኅጉሪቱ አማራጭ የፋይናንስ መሠረተ ልማትን ለመዘርጋት እና ከዶላር ጥገኝነት ለመውጣት የምታደርገውን እያደገ የመጣ ጥረት እንደሚያሳይ የንግድ እና የኢንቨስትመንት አማካሪው ከፈለኝ ኃይሉ ገልጸዋል።

"ይህን ጥገኝነት የመቀልበስ ፍላጎት ከፖለቲካ መፈክርነት ተሻግሯል…በመሠረቱ ለደህንነትም አስፈላጊ ሆኗል" ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

በፖለቲካዊ ቁርጠኝነት የታገዘው የብሪክስ የክፍያ ሥርዓት ውህደት ከሙከራ ደረጃ ወደ ትግበራ እየተሸጋገረ መሆኑን የገለጹት ባለሙያው፤ አፍሪካ ከአይኤምኤፍ እና በዶላር ከሚመሩ የብድር ሥርዓቶች ማምለጥ እንዳለባት አክለዋል።

"የአፍሪካ ሀገራት በዶላር በሚመሩ የብድር ደረጃ አውጪ ሥርዓቶች ላይ ያላቸውን ጥገኝነት ከቀጠሉ፤ የአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ክልላዊ የገበያ ትስስሮችን አደጋ ላይ ይጥላሉ" ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0