ፑቲን የኢኮኖሚ የስበት ማዕከል ‘ሊቀለበስ የማይችል ሽግግር’ ላይ እንደሚገኝ በ #SPIEF ጉባዔ ንግግራቸው በግልጽ አመልክተዋል - ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopiaፑቲን የኢኮኖሚ የስበት ማዕከል ‘ሊቀለበስ የማይችል ሽግግር’ ላይ እንደሚገኝ በ #SPIEF ጉባዔ ንግግራቸው በግልጽ አመልክተዋል - ባለሙያ
ፑቲን የኢኮኖሚ የስበት ማዕከል ‘ሊቀለበስ የማይችል ሽግግር’ ላይ እንደሚገኝ በ #SPIEF ጉባዔ ንግግራቸው በግልጽ አመልክተዋል - ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 06.06.2026
ሰብስክራይብ

ፑቲን የኢኮኖሚ የስበት ማዕከል ‘ሊቀለበስ የማይችል ሽግግር’ ላይ እንደሚገኝ በ #SPIEF ጉባዔ ንግግራቸው በግልጽ አመልክተዋል - ባለሙያ

“በምዕራባውያን ላይ ከማከለው የቀድሞው ሥርዓት ወደ ብዙኃን (ባለብዙ ዋልታ) መዋቅር” ከሚደረገው ጉዞ ጋር ተያይዞ “የፖለቲካ ኃይል” ሽግግርም እየመጣ መሆኑን ታዋቂው የፓኪስታን የፋይናንስ ተንታኝ ሰይድ ጃቪድ ሀሰን ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

“የወቅቱ ነውጥ ያልተለመደ ክስተት ሳይሆን ከአንድ ወገን ‘የበላይነት’ ሞዴል፤ በርካታ የዕድገት ማዕከላት በእኩል መሠረት አብረው ወደሚኖሩበትና ወደሚወዳደሩበት ሥርዓት የሚደረገው ሽግግር ተገማች ውጤት ነው።”

ፑቲን መልዕክታቸውን በግልፅ አስተላልፈዋል እንደ ሀሰን ገለጻ፡፡ የኢኮኖሚ ፀሐይ በምስራቅ እና በደቡብ ስጥወጣ፤ የቀድሞዎቹ ማዕከላት — አውሮፓ እና በተወሰነ ደረጃም አሜሪካ — በአንጻራዊነት አቅማቸውን እያጡ ነው።

“የዓለም ንግድ እና ፋይናንስ ትኩረት መዛወሩን በቀጠለበት ወቅት፤ ንግድ እና ካፒታል ይበልጥ ተስፋ ሰጪ ወደሆኑ አካባቢዎች እያዘነበሉ ነው። ይህ የኃይል ሚዛን መስተካከል በመጨረሻ ዓለም አቀፋዊው ሥርዓት ‘የበለጠ ፍትሐዊ’ እንዲሆን ያደርገዋል፤ ምክንያቱም የኢኮኖሚ ዕድገት በጥቂት የተለመዱ ኃያላኖች ብቻ ተከማችቶ ከመቅረት ይልቅ ለሰፊ ሀገራት ተደራሽ ይሆናል።”

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0