https://amh.sputniknews.africa/20260606/4251637.html
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ለሀገር ውስጥ አምራቾች የ4 ዓመት ነፃ የኢንዱስትሪ ፓርኮች አገልግሎት አመቻቸ
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ለሀገር ውስጥ አምራቾች የ4 ዓመት ነፃ የኢንዱስትሪ ፓርኮች አገልግሎት አመቻቸ
Sputnik አፍሪካ
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ለሀገር ውስጥ አምራቾች የ4 ዓመት ነፃ የኢንዱስትሪ ፓርኮች አገልግሎት አመቻቸ ይህ አዲስ ፖሊሲ የሀገር ውስጥ አምራቾችን ለመደገፍና የኢንዱስትሪ ልማትን ለማፋጠን ያለመ ነው። “አምራቾች በቀላሉ ወደ ምርት... 06.06.2026, Sputnik አፍሪካ
2026-06-06T17:52+0300
2026-06-06T17:52+0300
2026-06-06T17:54+0300
sputnik africa
telegram sputnik_ethiopia
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/img/07ea/06/06/4251484_0:0:1280:720_1920x0_80_0_0_a666f74c6f400f85443339dece33150e.jpg
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ለሀገር ውስጥ አምራቾች የ4 ዓመት ነፃ የኢንዱስትሪ ፓርኮች አገልግሎት አመቻቸ ይህ አዲስ ፖሊሲ የሀገር ውስጥ አምራቾችን ለመደገፍና የኢንዱስትሪ ልማትን ለማፋጠን ያለመ ነው። “አምራቾች በቀላሉ ወደ ምርት እንዲገቡ፣ የሥራ ዕድል እንዲፈጥሩ እንዲሁም ለውጭና ለሀገር ውስጥ ገበያ ምርቶችን እንዲያቀርቡ እንደግፋቸዋለን” ሲሉ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሰሃ ይታገሱ ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል። በአዲሱ ፖሊሲ መሠረት ብቁ የሆኑ ኢንተርፕራይዞች በተመረጡ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ለአራት ዓመታት ያህል ያለምንም ክፍያ እንዲሠሩ ማበረታቻ ይደረግላቸዋል። “በዋናነት የሀገራችንን ባለሀብቶች መደገፍ፣ ማበረታታት እንዲሁም ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ወደ መካከለኛና ትልቅ ኢንዱስትሪዎች እንዲያድጉ ማስቻል በጣም ወሳኝ ነው” ብለዋል። ኮርፖሬሽኑ በዚህ ተነሳሽነት የመጀመሪያ ምዕራፍ፤ ኤሌክትሪክ፣ ውሃ፣ ቴሌኮሙኒኬሽን እና የፍሳሽ ማስወገጃ መሠረተ ልማቶችን አሟልቶ፤ ለ26 መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች 10 ሄክታር መሬት አስተላልፏል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
2026
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ለሀገር ውስጥ አምራቾች የ4 ዓመት ነፃ የኢንዱስትሪ ፓርኮች አገልግሎት አመቻቸ
Sputnik አፍሪካ
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ለሀገር ውስጥ አምራቾች የ4 ዓመት ነፃ የኢንዱስትሪ ፓርኮች አገልግሎት አመቻቸ
2026-06-06T17:52+0300
true
PT1S
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/img/07ea/06/06/4251484_160:0:1120:720_1920x0_80_0_0_00092dac113f3d2bd11a4cf98006ba55.jpgSputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ለሀገር ውስጥ አምራቾች የ4 ዓመት ነፃ የኢንዱስትሪ ፓርኮች አገልግሎት አመቻቸ
17:52 06.06.2026 (የተሻሻለ: 17:54 06.06.2026) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ለሀገር ውስጥ አምራቾች የ4 ዓመት ነፃ የኢንዱስትሪ ፓርኮች አገልግሎት አመቻቸ
ይህ አዲስ ፖሊሲ የሀገር ውስጥ አምራቾችን ለመደገፍና የኢንዱስትሪ ልማትን ለማፋጠን ያለመ ነው።
“አምራቾች በቀላሉ ወደ ምርት እንዲገቡ፣ የሥራ ዕድል እንዲፈጥሩ እንዲሁም ለውጭና ለሀገር ውስጥ ገበያ ምርቶችን እንዲያቀርቡ እንደግፋቸዋለን” ሲሉ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሰሃ ይታገሱ ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል።
በአዲሱ ፖሊሲ መሠረት ብቁ የሆኑ ኢንተርፕራይዞች በተመረጡ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ለአራት ዓመታት ያህል ያለምንም ክፍያ እንዲሠሩ ማበረታቻ ይደረግላቸዋል።
“በዋናነት የሀገራችንን ባለሀብቶች መደገፍ፣ ማበረታታት እንዲሁም ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ወደ መካከለኛና ትልቅ ኢንዱስትሪዎች እንዲያድጉ ማስቻል በጣም ወሳኝ ነው” ብለዋል።
ኮርፖሬሽኑ በዚህ ተነሳሽነት የመጀመሪያ ምዕራፍ፤ ኤሌክትሪክ፣ ውሃ፣ ቴሌኮሙኒኬሽን እና የፍሳሽ ማስወገጃ መሠረተ ልማቶችን አሟልቶ፤ ለ26 መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች 10 ሄክታር መሬት አስተላልፏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X