በኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት 40 ሺህ ኪሎ ሜትር የሚጠጉ አዳዲስ መንገዶች ተገንብተዋል - የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር

ሰብስክራይብ

በኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት 40 ሺህ ኪሎ ሜትር የሚጠጉ አዳዲስ መንገዶች ተገንብተዋል - የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር

⬆ በየዓመቱ በአማካይ ከ8 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ አዳዲስ መንገዶች ተገንብተው፤ የሀገሪቱ የመንገድ ሽፋን ከ144 ሺህ ኪሎ ሜትር ወደ 182 ሺህ ኪሎ ሜትር ከፍ እንዳለ የሚኒስቴሩ ሚኒስትር ዴኤታ የትምጌታ አስራት ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ገልጸዋል፡፡

በተለይም ከ76 በላይ የሀገሪቱ ከተሞች የተተገበረው የኮሪደር ልማት የከተሞችን ገጽታ እንደቀየረ ተናግረዋል፡፡

“የመንገድ ግንባታዎች ከርዝመትና ከመጠን ባለፈ ለጥራትና ለውበት ከፍተኛ ዋጋ እየተሰጣቸው ነው፡፡ የተሠሩት መንገዶች ሰፊ የእግረኛና የሳይክል መንገዶችን፣ አረንጓዴ ስፍራዎችንና ዘመናዊ የመንገድ መብራቶችን ያካተቱ ናቸው” ብለዋል፡፡

ቪዲዮ፦ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0