በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነ የዘረመል፣ የፎሬንሲክና ስነምረዛ ምርመራ የልህቀት ማዕከል በአዲስ አበባ ተመርቆ ተከፈተ

ሰብስክራይብ

በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነ የዘረመል፣ የፎሬንሲክና ስነምረዛ ምርመራ የልህቀት ማዕከል በአዲስ አበባ ተመርቆ ተከፈተ

ዳግማዊ ምኒሊክ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ ውስጥ የተከተፈተው ይህ ማዕከል፤ ዘመናዊ አሠራርን ገቢር የሚያደርግ፣ ወጪና መዘግየትን የሚያስቀር እና ለፍትሕ ምርመራ ውጤታማነት ጉልህ ሚና እንደሚጫወት ተነግሯል።

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፤ "ማዕከሉ ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት ከመስጠት ባለፈ፤ ለሀገሪቱ አክሞ የማዳን ተግባርና በዘርፉ ባለሙያዎችን ለማሠልጠን ትልቅ ተደማሪ አቅም ይሆናል" ብለዋል።

አዲስ የተመረቀው የፎረንሲክ፣ የዘረ-መል እና የስነ-ምረዛ የልህቀት ማዕከል፤ ለህብረተሰቡና ለፍትሕ ስርዓቱ በአንድ መስኮት የተደራጀና የተቀላጠፈ አገልግሎት መስጠት ያስችላል ተብሏል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0