ዋልያዎቹ ዛሬ ከነበልባሎቹ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ እየተጠበቀ ነው
10:48 06.06.2026 (የተሻሻለ: 11:34 06.06.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ዋልያዎቹ ዛሬ ከነበልባሎቹ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ እየተጠበቀ ነው
የኢትዮጵያ እና ማላዊ ብሔራዊ ቡድኖች ዛሬ 12፡00 ላይ እና በመጪው ማክሰኞ በድሬዳዋ ስታዲየም፤ ዓለም አቀፍ የወዳጅነት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
ስለዋልያዎቹ ተፋላሚዎች ጥቂት መረጃ፦
◻ በቅጽል ስሙ ነበልባሎቹ ተብሎ የሚጠራው የማላዊ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ሦስት ገዜ ተሳትፏል፡፡
◻ ትልቁ ስኬቱ ካሜሩን ባዘጋጀችው የ2013ቱ አፍሪካ ዋንጫ ለጥሎ ማለፍ መብቃቱ ነው፡፡
◻ የሴካፋ ዋንጫን ሦስት ግዜ (እ.አ.አ 1978፣1979 እና 1988) አንስቷል፡፡
የእርስ በርስ ግንኙነት፦
◻ ኢትዮጵያ አንድ ግዜ ስታሸንፍ፤ ማላዊ ሁለት ግዜ ድል ተቀዳጅታለች፡፡
◻ ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ሦስት ገዜ አቻ ወጥተዋል፡፡
ኢትዮጵያ እና ማላዊ እስካሁን በዓለም ዋንጫ ካልተሳተፉ የአፍሪካ ሀገራት መካከል ናቸው፡፡
የሁለቱ ሀገራት የወዳጅነት ጨዋታ፤ ለ2019 የአፍሪካ ዋንጫ ማጠሪያ የሚደርጉት ዝግጅት አካል ነው፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia