"የሩሲያ የዶንባስ ቁጥጥር እና ከዩክሬን ጋር ስምምነት ላይ መድረስ እርስ በርሳቸው አይጋጩም" – ፑቲን
"የሩሲያ የዶንባስ ቁጥጥር እና ከዩክሬን ጋር ስምምነት ላይ መድረስ እርስ በርሳቸው አይጋጩም" – ፑቲን
የሩሲያው ፕሬዝዳንት በሴንት ፒተርስበርግ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ፎረም ከዓለም አቀፍ የዜና ወኪሎች ኃላፊዎች ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት የሰጧቸው ተጨማሪ መግለጫዎች፦
የዩክሬን የጦር ኃይሎች በከፍተኛ ሁኔታ የሰው ኃይል እጥረት አለበት፤ በቅርቡ የዩክሬን የጦር ኃይሎች ቁጥር በ100 ሺህ ሲቀንስ፣ በየወሩ ደግሞ 40 ሺህ ያጣል።
በዩክሬን ያለው አስገዳጅ የውትድርና ምልመላ በወር ከ15, ሺህ እስከ 16 ሺህ የሚሆኑ ሰዎቹን የሚያስገኝ ሲሆን፣ እነዚህም ሰዎች "እንደ ውሻ የተያዙ" ናቸው።
በልዩ ወታደራዊ ዘመቻው ውስጥ የሩሲያ ጦር ኃይሎች ጥቃት የማያካሂዱበት ምንም ቦታ የለም።
ሩሲያ የሉሃንስክ ሕዝባዊ ሪፐብሊክን ግዛትን ሙሉ በሙሉ እንዲሁም ከዶኔትስክ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ግዛት ደግሞ ከ85% በላይ የሚሆነውን በቁጥጥሯ ሥር አውላለች።
ሩሲያ የአየር መቃወሚያ ሥርዓቷን ታጠናክራለች፤ ሩሲያ እነዚህ ሥርዓቶች አሏት፤ ዩክሬን ግን መሰል ሥርዓት የላትም።
ክፍሎቹ (ግንቦቹ) እንዴት እንደሚወድቁ ለማየት "ኦሬሽኒክ" በዩክሬን የሚገኝን አንድ "ጎተራ" (ማከማቻ) መቷል፤ ይህም ለጦር መሣሪያውን የወደፊት አጠቃቀም በጣም አሰፈላጊ ነው፡፡
ፑቲን ወደፊት "ኦሬሽኒክ" ሚሳኤል በከተማ አካባቢዎች የሚገኙትን ጨምሮ በተለያዩ ኢላማዎች ላይ በሙሉ አቀም ለመጠቀም ውሳኔዎች ሊተላለፉ እንደሚችሉ አልሸሸጉም።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X