በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት የተለዋጭ አባልነት ወንበር ምርጫን ማሸነፍ ለዚምባብዌ ‘ታሪካዊ ምዕራፍ’ ነው - የአገሪቱ ሚኒስትር

ሰብስክራይብ

በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት የተለዋጭ አባልነት ወንበር ምርጫን ማሸነፍ ለዚምባብዌ ‘ታሪካዊ ምዕራፍ’ ነው - የአገሪቱ ሚኒስትር

የነፃነት ትግል አርበኞች ጉዳይ ሚኒስትር ሞኒካ ማቭሁጋ ለስፑትኒክ አፍሪካ እንደተናገሩት፤ ይህ ስኬት አገሪቱ በዓለም አቀፍ የውይይት መድረኮች ላይ ያላትን አቋም በአዎንታዊ መልኩ ይቀርጻል።

ከተመድ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፤ ይህች የአፍሪካ አገር እ.ኤ.አ. በጥር 2027 ለሁለት ዓመታት በምክር ቤቱ ውስጥ ወንበራቸውን ከሚረከቡት አምስት አገራት መካከል አንዷ ናት።

ምክር ቤቱ በቋሚ አባላቱ መካከል ቀጣይነት ባለው ክፍፍል ውስጥ ባለበት በአሁኑ ወቅት ዚምባብዌ የሥራ ዘመኗን ለማገልገል መዘጋጀቷን ድርጅቱ አመላክቷል።

የጸጥታው ምክር ቤት በ15 አባላት የተዋቀረ ሲሆን፤ እነሱም፦ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት (ቬቶ) ያላቸው አምስት ቋሚ አባላት (ሩሲያ፣ ቻይና፣ ፈረንሳይ፣ አሜሪካ እና ብሪታንያ) እና አሥር ተለዋጭ (ቋሚ ያልሆኑ) አባላት ናቸው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0