የሩሲያ ቋንቋ በሰው ልጅ የባሕል ቅርስ ውስጥ የላቀ ቦታ አለው፦ የዩኔስኮ የኢትዮጵያ ተጠሪ

© telegram sputnik_ethiopiaየሩሲያ ቋንቋ በሰው ልጅ የባሕል ቅርስ ውስጥ የላቀ ቦታ አለው፦ የዩኔስኮ የኢትዮጵያ ተጠሪ
የሩሲያ ቋንቋ በሰው ልጅ የባሕል ቅርስ ውስጥ የላቀ ቦታ አለው፦ የዩኔስኮ የኢትዮጵያ ተጠሪ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 04.06.2026
ሰብስክራይብ

የሩሲያ ቋንቋ በሰው ልጅ የባሕል ቅርስ ውስጥ የላቀ ቦታ አለው፦ የዩኔስኮ የኢትዮጵያ ተጠሪ

የታላቁ የሩሲያ ገጣሚ አሌክሳንደር ፑሽኪን በተወለደበት እለት በየዓመቱ በሚከበረው የዓለም የሩሲያ ቋንቋ ቀን ላይ ንግግር ያደረጉት፤ በኢትዮጵያ በኢትዮጵያ የዩኔስኮ የግንኙነት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሪታ ቢሱናውት እንዳሉት፣ የደራሲው የሥነ-ጽሑፍ ቅርስ በትውልዶች እና በአኅጉራት መካከል ያሉ አንባቢዎችን ማነሳሳቱን ቀጥሏል።

ሪታ ቢሱናውት፣ የሩሲያ ቋንቋ በሳይንስ፣ በፍልስፍና፣ በዲፕሎማሲ እና በኪነ-ጥበብ ፈጠራ ለዓለም ሥልጣኔ የላቀ አስተዋፅዖ በማበርከት የሰው ልጅ የባሕል ቅርስ ውስጥ የላቀ ቦታ አለው ብለዋል፡፡

"በፑሽኪን፣ ቶልስቶይ፣ ዶስቶየቭስኪ፣ ቼኮቭ እና በሌሎችም በርካታ ደራሲያን ሥራዎች አማካኝነት የሩሲያ ስነ-ጽሑፍ ስለ ሰው ልጅ ክብር፣ ነፃነት፣ ፍትሕ እና ኃላፊነት የሚነሱ ዘላቂ ጥያቄዎችን መርምሯል። መልስም ሰጥቷል፡፡” ማለታቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠና ዘግቧል።

ከሥነ-ጽሑፍ ባሻገር የሩሲያ ቋንቋ ለሳይንሳዊ ምርምር፣ ለከፍተኛ ትምህርት፣ ለፈጠራ እና ለዓለም አቀፍ ትብብር ጠቃሚ ቋንቋ ሆኖ መቀጠሉን ኃላፊዋ አስረድተዋል።

ሪታ ቢሱናውት፣ የሩሲያ ቋንቋ ሕያው ሆኖ እንዲቀጥልና እንዲተላለፍ ለሚያደርጉ መምህራን፣ ተመራማሪዎች፣ ተርጓሚዎች፣ ጸሐፊዎች፣ አርቲስቶች እና ለሚሊዮኖች ተናጋሪዎች ክብር ሰጥተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0