ሩሲያኛ ከሥነ-ጽሑፍ እና ፍልስፍና ባሻገር የሳይንስ እና የፈጠራ ቋንቋ ነው - የተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ምክትል ዋና ጸሐፊ
17:04 04.06.2026 (የተሻሻለ: 17:14 04.06.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሩሲያኛ ከሥነ-ጽሑፍ እና ፍልስፍና ባሻገር የሳይንስ እና የፈጠራ ቋንቋ ነው - የተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ምክትል ዋና ጸሐፊ
ማማ ኬታ፣ “ውስብስብ በሆኑ ዓለም አቀፍ ፈተናዎች በተሞላችው በዛሬዋ ዓለም፣ ብዙ ቋንቋዎችን የመጠቀም ባህል ከምንጊዜውም በላይ የተባበሩት መንግስታት ስርዓት መሠረታዊ እሴት ሆኖ ቀጥሏል። ይህም በሀገራት መካከል ለውይይት፣ ሁሉንም አካታች ለሆነ ግንኙነት፣ ለጋራ መከባበር እና ለትብብር ወሳኝ መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል።” ብለዋል።
በመጪው ቅዳሜ ግንቦት 29 የሚከበረውን የሩሲያ ቋንቋ ቀን በሚዘክረው መረሃግብር የተባበሩት መንግሥታት ኃላፊዎች፣ የተለያዩ ሃገራት አምባሳደሮች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች፣ ምሁራን እና ተማሪዎች በተገኙበት ዛሬ አዲስ አበባ በሚገኘው የአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን ተከብሯል።
በዝግጅቱ ላይ ጸሐፌ ተውኔት እና ባለቅኔ አያልነህ ሙላቱን ጨምሮ ሌሎች ታላላቅ የኢትዮጵያ የሥነ ጽሑፍ ሰዎች፣ የታዋቂው ሩሲያዊ የሥነ ጽሑፍ ሰው አሌክሳንደር ፑሽኪን ሥራዎችን ማቅረባቸውን ሁነቱን የታደመው የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል፡፡
በዝግጅቱ ላይ ስለቀረቡ ይዘቶች ተጨማሪ መረጃዎችን ለምግኘት ቪዲዮውን ይመልከቱ፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X