የኢትዮጵያ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ፦ አኅጉሪቱ ከምርጫው ምን ትቅሰም? የአፍሪካ ሕብረት ታዛቢዎች ምክረ ሐሳባቸውን አጋርተዋል፦
የኢትዮጵያ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ፦ አኅጉሪቱ ከምርጫው ምን ትቅሰም? የአፍሪካ ሕብረት ታዛቢዎች ምክረ ሐሳባቸውን አጋርተዋል፦
ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ የተካሄደውን ጠቅላላ ምርጫ የታዘበው የአፍሪካ ህብረት የልዑካን ቡድን የመጀመሪያ ደረጃ የግምገማ ውጤት መግለጫውን ዛሬ ይፋ አድርጓል። ህብረቱ በነበረው ሂደት ላይ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ሊቀስሟቸው የሚገቡ "የሚደነቁና አርአያነት ያላቸው ልምዶች" በማለት የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች በምሳሌነት አንስቷል፦
የፀጥታ አካላት ሙያዊ ብቃት፦ የፓሊስና የፀጥታ አካላት ከምርጫ ጣቢያዎች ተገቢውን ርቀት ጠብቀው በመቆም፣ ያለ ምንም ጣልቃ ገብነትና ማስፈራራት መራጩ ህዝብ በነፃነት ድምፁን እንዲሰጥ ሰላማዊ አካባቢ ፈጥረዋል።
የምርጫ አስፈፃሚዎች ቁርጠኝነት፦ አስፈፃሚዎች ሕግና መመሪያዎችን ጠብቀው የታማኝነትና ተአማኒነት ማረጋገጫ ሂደቶችን በብቃት ተግብረዋል። የድምፅ መስጫ ሰዓት በተራዘመበት ወቅትም በከፍተኛ ትጋት ህዝቡን ሲያገለግሉ ተስተውለዋል።
የዜጎች ንቁ ተሳትፎና ባህላዊ እሴቶች፦ በምርጫ ጣቢያዎች የሀገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ በክብር መውለብለቡና የአካባቢው ባህላዊ እሴቶች መካተታቸው ብሔራዊ ኩራትን አሳይቷል። በአንዳንድ ቦታዎችም ዜጎች በሰልፍ ላይ ለነበሩ መራጮች ምግብ ነክና ውሃ በማቅረብ የመደጋገፍ ሰላማዊ ድባብ ፈጥረዋል።
ፈጣንና ምላሽ ሰጪ አሰራር፦ የድምፅ መስጫ ሳጥኖች በሞሉባቸው ጣቢያዎች ላይ የምርጫ አስፈፃሚዎች ወዲያውኑ ተጨማሪ ሳጥኖችን በማቅረብ ሂደቱ ሳይስተጓጎል እንዲቀጥል አድርገዋል።
የሀገር ውስጥ ታዛቢዎች ሚና፦ የሴቶችና የወጣቶች ማኅበራትን ጨምሮ የሀገር ውስጥ ታዛቢዎች በስፋት መሳተፋቸው ለምርጫው ግልፅነትና ተአማኒነት ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክቷል።
የቁሳቁስ አቅርቦት ውጤታማነት፦ ሀገሪቱ ሰፊ ከመሆኗና ካጋጠሙ የሎጂስቲክስ ፈተናዎች አንጻር፣ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስፈላጊ ቁሳቁሶችን በሁሉም ጣቢያዎች በወቅቱ ማድረሱ የተሳካ እቅድና ቅንጅት እንደነበረ አሳይቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X