የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ልዑካን ቡድን ከርዕሰ ብሔር ታዬ አጽቀሥላሴ ጋር ውይይት አደረገ

© telegram sputnik_ethiopiaየሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ልዑካን ቡድን ከርዕሰ ብሔር ታዬ አጽቀሥላሴ ጋር ውይይት አደረገ
የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ልዑካን ቡድን ከርዕሰ ብሔር ታዬ አጽቀሥላሴ ጋር ውይይት አደረገ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.06.2026
ሰብስክራይብ

የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ልዑካን ቡድን ከርዕሰ ብሔር ታዬ አጽቀሥላሴ ጋር ውይይት አደረገ

ርዕሰ ብሔር ታዬ በሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት መምሪያ የበላይ ኃላፊ ብፁዕ አቡነ አንቶኒዮስ የተመራው ልዑካን ቡድን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ብፁዕ አቡነ አንቶኒዮስ ከፕሬዝዳንቱ ጋር የተሳካ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸው፤ በሩሲያ እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለው ግንኙነት በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናትም ሆነ ለሀገራቱ ዘላቂ ወዳጅነት ትልቅ ማረጋገጫ መሆኑን ጠቁመዋል።

በውይይቱ የተሳተፉት የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት እንዲሁም የደቡብ ኦሞ እና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ በበኩላቸው፣ ይህ መንፈሳዊና ባህላዊ ትስስር በሕዝብ ለሕዝብ ዲፕሎማሲ ላይ በቅንጅት ለመሥራት የጎላ ፋይዳ እንዳለው አስረድተዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ተርኪንና ሌሎች የልዑኩ አባላት ተገኝተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopiaየሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ልዑካን ቡድን ከርዕሰ ብሔር ታዬ አጽቀሥላሴ ጋር ውይይት አደረገ
የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ልዑካን ቡድን ከርዕሰ ብሔር ታዬ አጽቀሥላሴ ጋር ውይይት አደረገ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.06.2026
አዳዲስ ዜናዎች
0