የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት መምሪያ ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ አንቶኒዮስ አዲስ አበባ ገቡ
20:10 03.06.2026 (የተሻሻለ: 20:14 03.06.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት መምሪያ ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ አንቶኒዮስ አዲስ አበባ ገቡ
የሞስኮና የመላው ሩሲያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል በሰጡት ቡራኬና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ግብዣ መሠረት፤ የሞስኮ ፓትርያርክ የውጭ ግንኙነት መምሪያ የበላይ ኃላፊ ብፁዕ አቡነ አንቶኒዮስ ዛሬ ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ ገብተዋል።
ብፁዕነታቸው ወደ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ያቀኑ ሲሆን፤ በሩሲያና በኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለውን የውይይት ኮሚሽን በጋራ በሚመሩት በደቡብ ኦሞ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ፣ በፓትርያርኩ ልዩ ተወካይ በቆሞስ አባ ዳንኤል ሰይፈሚካኤልና በካቴድራሉ ሊቃውንት ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ብፁዕ አቡነ አንቶኒዮስ በኢትዮጵያ በሚቆዩባቸው ሦስት ቀናት ውስጥ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣ ከኢፌዴሪ ከፍተኛ የመንግሥት መሪዎችና በኢትዮጵያ ከሚኖሩ የሩሲያ ዜጎች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

1/6
© telegram sputnik_ethiopia

2/6
© telegram sputnik_ethiopia

3/6
© telegram sputnik_ethiopia

4/6
© telegram sputnik_ethiopia

5/6
© telegram sputnik_ethiopia

6/6
© telegram sputnik_ethiopia
1/6
© telegram sputnik_ethiopia
2/6
© telegram sputnik_ethiopia
3/6
© telegram sputnik_ethiopia
4/6
© telegram sputnik_ethiopia
5/6
© telegram sputnik_ethiopia
6/6
© telegram sputnik_ethiopia